Saturday, 17 July 2021 15:45

ቀበጧ አማፂ

Written by  ዘውድአለም ታደሠ
Rate this item
(0 votes)

     (አማን መዝሙር)
አማራ ክልል ብአዴን በየአመቱ ስብሰባ ሲያደርግ የህወኃት ሰዎች ይገኛሉ። ለነሱ ደስታ ሲባል ብአዴኖች ግድግዳው ላይ «ትምክህተኝነትን እንጠየፋለን» የሚል ፅሁፍ ይለጥፋሉ። ህወኃት’ኮ ትምክህተኛ የምትለው የአማራን ህዝብ ነው
አንድ ጊዜ ለኦሮሚያ ፕሬዚዳንት የሚሆን ሰው የኔ ዘመዶች መርጠው ወደ መለስ አመጡ። መሌ የሰውዬውን ስም ሲመለከት «አልተመቸኝም ቀይሩት» ብሎ ላከ። ኦህዴዶች አላቅማሙም፤ ድጋሚ ፕሬዚዳንት ተቀየረ። ምፅ ምፅ !
ሱማሌ ክልል ምክር ቤት ስብሰባ ሲደረግ የግድ የህወኃት ሰዎች ይገኛሉ። እነሱ ታዲያ ሱማሊኛ ስለማይችሉ ስብሰባው በአማርኛ ይደረግ ነበር
እግዜር ያሳያችሁ፤ የዛሬዋ አማፂ የትናንቷ ልእለ ሃያል መንግስት ህወኃት ከዚህ አይነት ከባድ power ወርዳ ነው ዛሬ አንድ የአማራ ክልል መኪና ሰረቅሁ ብላ ፎቶ የምትለቀው። እንዲህ ያለ ነገር በዘራችሁ አይድረስ!


Read 2101 times