Print this page
Saturday, 17 July 2021 14:30

“የአውሮፕላን የበረራ ምስጢሮች” ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

     የታዳጊው ቅዱስ የሺዋስ “የአውሮፕላን የበረራ ምስጢሮች” መፅሀፍ ዛሬ ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡
በእድሜው ትንሽ የሆነው ታዳጊ አጠቃላይ የአውሮፕላን በረራ ሂደቶችና ምስጢራትን በመጽሀፉ የዳሰሰ ሲሆን በዚህ ዕድሜው መፅሀፍ መፃፉም ለዕድሜ እኩዮቹ መነቃቃት ይፈጥራል ተብሏል፡፡
በምረቃው ዕለት አብራሪዎች የአውሮፕላን ጠጋኞችና በርካታ ምሁራን የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፣ መጋቢ አዲስ እሸቱ ዓለማየሁ፣ የፍልስፍና ምሁር ዮናስ ዘውዴ፣ ወ/ሮ ፍሬ ዓለም ሽባባው፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ፣ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ካፒቴን ሰለሞን ግዛው፣ የአውሮፕላን ቴክኒሽያኑ ኤሊያስ አብራር፣ የደራሲ ቅዱስ የሺዋስ የእድሜ  እኩዮችና በህዋ ሳይንስ ላይ  አስደናቂ እውቀት የሚታወቀውን ታዳጊ ሮቤል በአምላክን ጨምሮ ታዳጊ ቅዱስ ዕንቁ ባህሪ፣ ታዳጊ ዲሜጥሮስ ተመስገንና ታዳጊ ሙሳ ከድር ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ የምርቃቱ አዘጋጅ ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት አስታውቋል፡፡


Read 1015 times