Print this page
Tuesday, 13 July 2021 00:00

አይስላንድ ከአለማችን አገራት በደህንነት ቀዳሚነቱን ይዛለች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የአገራትን አጠቃላይ ሁኔታ በመገምገም በየአመቱ የአገራትን የሰላምና ደህንነት ደረጃ የሚያወጣው ግሎባል ፋይናንስ መጽሄት ከሰሞኑ የ2021 ሪፖርቱን ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ አስላንድ ደህንነት በእጅጉ የሰፈነባት ቀዳሚዋ የአለማችን አገር ተብላለች፡፡
134 የአለማችን አገራት በተካተቱበት በዘንድሮው የግሎባል ፋይናንስ ሪፖርት በደህነነት የሁለተኛነት ደረጃን የያዘችው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ስትሆን፣ ኳታር፣ ሲንጋፖር፣ ፊላንድ፣ ሞንጎሊያ፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ካናዳ እና ኒውዚላንድ እንደቅደም ተከተላቸው ከሶስተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከ134 የአለማችን አገራት መካከል በደህንነት የመጨረሻውን ደረጃ የያዘችው ፊሊፒንስ ስትሆን፣ ኮሎምቢያ፣ ጓቲማላ፣ ናይጀሪያ፣ ቦስኒያና ሄርዘጎቪኒያ፣ ብራዚል፣ ሜክሲኮ፣ ፔሩ፣ የመንና ሰሜን ሜቄዶኒያ ይከተሏታል፡፡
ግሎባል ፋይናንስ መጽሄት የአገራትን የደህንነት ሁኔታ ከሚገመግምባቸው መስፈርቶች መካከል የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ፣ የጦርነትና የእርስ በእርስ ግጭቶች ክስተቶች፣ የግለሰቦች ደህንነት፣ የወንጀል ድርጊቶች፣ ሽብርተኝነትና ለተፈጥሮ አደጋ የመጋለጥ ዕድል እንደሚገኙበት የተነገረ ሲሆን፣ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ መስፈርት ሆኖ መቅረቡንና ይህም በአገራት የደህንነት ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት መቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2654 times
Administrator

Latest from Administrator