Sunday, 11 July 2021 17:28

በቶኪዮ 2020

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

 ከ32ኛው ኦሎሚፒያድ በፊት ኢትዮጵያ  ከተሳተፈችባቸው 13 ኦሎምፒያዶች ከአንድ በላይ ሜዳሊያ በመሰብሰብ ከፍተኛውን ውጤትን ያስመዘገበችው ጥሩነሽ ዲባባ ስትሆን 6 ሜዳሊያዎችን (3 የወርቅ 3 የነሀስ) በመሰብሰብ ነው፡፡ ቀነኒሳ በቀለ በ4 ሜዳሊያዎች (3 የወርቅና 1 የብር) 2ኛ ደረጃ ሲይዝ፤ምሩፅ ይፍጠር በ3 ሜዳሊያዎች (2 የወርቅና 1 የነሐስ)፤ ደራርቱ ቱሉ በ3 ሜዳሊያዎች (2 የወርቅና 1 የነሐስ) እንዲሁም መሰረት ደፋር በ3 ሜዳልያዎች (2 የወርቅ 1 የነሀስ)፤ እኩል 3ኛ ደረጃን ይጋራሉ፡፡ ማሞ ወልዴ 3 ሜዳልያዎችን (1 የወርቅ፣ 1 የብርና 1 የነሀስ)፤ ጌቴ ዋሚ በ3 ሜዳሊያዎች (1 የብር፣ 2 የነሀስ)፣ አበበ ቢቂላ 2 ሜዳልያዎችን (የወርቅና 1 የነሀስ)፤ ኃይሌ ገ/ሥላሴ በ2 ሜዳልያዎች (2 የወርቅ፣) አልማዝ አያና በ2 ሜዳልያዎች (1 የወርቅና 1 የነሀስ) እንዲሁም ስለሺ ሰህን በ2 ሜዳሊያዎች (2 የብር) ተከታታይ ደረጃዎች ይወስዳሉ፡፡
 ፋጡማ ሮባ፣ ገዛኸኝ አበራ፣ ሚሊዮን ወልዴ፣ ቲኪ ገላና እና አልማዝ አያና እያንዳንዳቸው 1 ወርቅ ሜዳ ላይ ያሸነፉ ናቸው፡፡  እጅጋየሁ ዲባባ፣ ደጀኔ ገብረመስቀል፣ ሶፊያ አሰፋ፣ ገንዘቤ ዲባባ እና ፈይሳ ሌሊሳ እያንዳንዳቸው 1 የብር ሜዳሊያ ያሸነፉ ሲሆኑ፤ መሀመድ ከድር፣ እሸቱ ቱራ፣ ፊጣ ባይሳ፣ አዲስ አበበ፣ አሰፋ መዝገቡ፣ ፀጋዬ ከበደ፣ ተስፋዬ ቶላ፣ ታሪኩ በቀለ፣ አበባ አረጋዊ፣ ታምራት ቶላ፣ ታሪኩ በቀለ፣ አበባ አረጋዊ፣ ታምራት ቶላ፣ ማሬ ዲባባ እና ሐጎስ ገብረህይወት ደግሞ እያንዳንዳቸው 1 የነሀሴ ሜዳልያ ተጎናጽፈዋል፡፡

Read 1737 times