Saturday, 03 July 2021 20:50

ጋዜጠኛ ካሳሁን አሰፋ ዛሬ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይዘከራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ባህርዳር ለእምቦጭ ነቀላ ከዳኞቹ ጋር የተጓዘውና በደረሰበት የስትሮክ በሽታ ህይወቱ ያለፈው ጋዜጠኛና ዲያቆን ካሳሁን አሰፋ 1ኛ የሙት አመት መታሰቢያው ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይዘከራል፡፡ በዕለቱ በዕድሜው የሰራቸው አጠቃላይ ስራዎች በዘጋቢ ፊልም ለታዳሚያን የሚቀርቡ ሲሆን፣ ወዳጆቹ፣ ጓደኞቹና የስራ ባልደረቦቹ በመድረኩ ስለ ጋዜጠኛ ካሳሁን ያላቸውን ስሜት ይገልፃሉ ይመሰክራሉም ተብሏል፡፡
የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶዎች፣ ግጥምና መሰል ኪነ-ጥበባዊ ስራዎች የሚቀርቡ ሲሆን ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመድ፣ የስራ  ባልደረቦቹ የመንግስት ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙም የመርሃ ግብሩ አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡
ጋዜጠኛና ዲያቆን ካሳሁን አሰፋ በብስራት 101.1 ሬዲዮ “አሻም” የተሰኘ በማህበራዊ፣ በባህልና በቱሪዝም በአጠቃላይ በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ የሚያጠነጥን የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ ሲሆን ከዚያ ቀደም መምህር፣ የፋና FM 89.1 ሬዲዮ ሲመሰረት የነበረ፣ የማስታወቂያ ባለሙያና ዘርፈ ብዙ የኪነ-ጥበብና የባህል ሰውም ነበር። በመንፈሳዊነት ታንጾ ያደገውና በድቁና ቤተክርስቲያንን ሲያገለግል የነበረው ጋዜጠኛ ካሳሁን ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች አባት የነበረ ሲሆን አገሩን ወዳድና ተቆርቋሪም ነበር።


Read 11403 times