Saturday, 03 July 2021 20:50

“ያላሻገረን ዲሞክራሲ” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  በደራሲ ምንተስኖት ጢቆ ነዲ የተሰናዳውና የኢትዮጵያን የ3 ሺህ ዓመት ጉዞ ይፈትሻል የተባለው “ያላሻገረን ዲሞክራሲ” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መፅሐፉ በዋናነት ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን ታሪኳ ከስልጣኔ፣ ከእድገትና፣ ከዲሞክራሲ እስካሁን የተኳረፈችበትን፣ የሚገኙ ጥሩ አጋጣሚዎች በእውቀት ማጣት የሚመክኑበትንና እስካሁን ለዘለቅንበት ሽኩቻ፣ መጠፋፋት፣ መጠላለፍና ወደኋላ የመጎተት አባዜዎችን በጥልቀት ይፈትሻል ተብሏል፡፡ በመፅሐፉ ጀርባ አስተያየት ያሰፈሩት የፍልስፍናና የነገረ መለኮት ተመራማሪው ዶ/ር ዮናስ ዘውዴም ይህንኑ ሀሳብ አስፍረውታል፡፡ ሌላው የታሪክና የህግ ምሁር አልማው ክፍሌ (ዶ/ር)”… ይህንን መፅሐፍ ስታነቡ ከስደት ከተመለሰው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት ጀምሮ እስከ ህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ፍፃሜ ድረስ የነበረውን የኢትዮጵያ የሽኩቻና የሴራ ፖለቲካ ለመመልከት ትችላላችሁ” በማለት አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡ በአምስት ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ226 ገፅ የተቀነበበው መጽሐፉ በ250 ብር እና በ25 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡



Read 11503 times