Sunday, 27 June 2021 16:37

በኢትዮጵያ የብሔራዊ መግባባት ውይይት እንዲካሄድ እንግሊዝን ጨምሮ 13 አገራት ጥሪ አቀረቡ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

ምርጫው ለዲሞክራሲያዊ ሽግግር አጋዥ ነው”
 
     “የእንግሊዝን መንግስት ጨምሮ 13 አገራት የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ሽግግር እንደሚደገፉ ገልፀው ምርጫ ብቻውን ዲሞክራሲያዊ ሽግግር አያመጣም ብሔራዊ መግባባት የሚፈጥሩ ውይይቶች ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡
የእንግሊዝ፣ካናዳ፣ጀርመን፣ጃፓን፣ኖርዌይ፣አውስትራሊያ፣ዴንማርክ፣ኔዘርለላንድ፣ኒውዝላንድና አየርላንድ መንግስት በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ ሰኔ 14 ቀን 2013 የተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ በብዙ  እንከኖች የተሞላ ቢሆንም ህብረተሰቡ ለምርጫው ያሳየው ተነሳሽነትና ተሳትፎ ለሃገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል፡፡
ምንም እንኳ ምርጫው በተገደበ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የተካሄደ ቢሆንም፣ በተለይ የሲቪክ ማህበራ ስለ ምርጫው ዜጎችን ለማንቃት ያደረጉት ጥረት በቀላሉ የሚታይ አለመሆኑን ሃገሪራቱ በእንግሊዝ ኢምባሲ በኩል በጋራ ባወጡት መግለጫቸው አመልክተዋል፡፡
በምርጫው ዜጎች በስፋት የተሳተፉ ቢሆንም፣ ነፃትን የሚያሳጡ አስጨናቂ ሁኔታዎች እንደነበሩበት የጠቆመው መግለጫው፤ በምርጫው እለትም የፖለቲካ ፓርቲ ተወካይ ታዛቢዎች መደብደባቸውንና ሂደቱን እንዳይታዘቡ የማድረግ ሁኔታዎች መስተዋላቸውን አውስተው፤ በቀጣይ ሃገሪቱ በምታደርገው የዴሞክራሲ ሽግግር ውስጥ እነዚህን ተግባራት ለማረም ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የዘንድሮው ምርጫ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ለሃገሪቱ የዲሞክራሲ ሽግግር አጋዥ ነው ያለው የሃገራቱ መግለጫ፤ ከዚህ በተጨማሪ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችሉ  ውይይቶች በፖለቲከኞች መካከል መካሄድ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይ በሃገሪቱ ለሚካሄድ ብሔራዊ መግባባት አዋጭ ውይይቶችንም እንደሚደገፉ ሃገሪቱ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡


Read 9584 times