Sunday, 27 June 2021 16:27

ባልደራስ 6ኛው አገራዊ ምርጫ፤ የምርጫ ዝቅተኛ መመዘኛን አያሟላም አለ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

 “በጥናት የደረስኩበትን ቦርዱ ውጤቱን ከገለፀ በኋላ ለህዝቡ ይፋ አደርጋለሁ”
     
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ፤ 6ኛው አገራዊ ምርጫ፤ የምርጫን ዝቅተኛ መመዘኛ የማያሟላ ነው ሲል ገለፀ፡፡
ፓርቲው ከምርጫው በፊት በምርጫው ወቅትና ከምርጫው በኋላ ባሉ ጉዳዮች ላይ ጥናት ማድረጉንና በጥናቱ ውጤትም ሰኔ 14 የተካሄደው ምርጫ ዝቅተኛ የምርጫ መመዘኛዎችን ያላሟላ ሆኖ ማግኘቱን ጠቁሟል፡፡ “
አዲስ አበባን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው” በሚል መሪ ቃል ሲንቀሳቀስ የነበረው  ፓርቲው፤ ከምርጫው በፊት በምርጫው ወቅትና ከምርጫው በኋላ በተለያዩ ሁኔታዎች ጫና እየተደረገበት መቆየቱን በጥናት የደረሰበትን ሃሳቤን በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ ማስቀመጥ ችያለሁ ብሏል፡፡
6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ፤ ከምርጫው በፊት ጀምሮ የተለያ ችግሮች ነበሩበት ያለው ፓርቲው፤ በመራጭ ምዝገባ ወቅት ያልነበሩና አዳዲስ ጣቢያዎች መከፈት፣ በድምፅ አሰጣጥ ስርዓቱ ወቅት የተስተዋሉ የተለያዩ ችግሮችና በፓርቲው አባላትና ታዛቢዎች ላይ ይደርሱ የነበሩ እንግልቶችን በማሳያነት ጠቅሷል፡፡
እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተም ሰፋ ያለ ትንተና እያካሄድ መሆኑንና የምርጫው ውጤት በቦርዱ ከተገለፀ በኋላ በጥናት የደረሰበትን  ውጤት ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡


Read 840 times