ህዝብ በነቂስ ወጥቶ - አምርሮ ሲያዝን ክፉኛ
መሪ ሲያስለቅስ እንጂ - አላየሁ ሲለቀስለት
እንዴት አድርጌ ልመን - ይህንን ዱብ ዕዳ ክስተት
ጐበዝ ተማር ከዚህ ሰው - የአገር መሲህ ነው በእውነቱ
ራሱን አቅልጦ አለፈ - ልክ እንደ ሻማ በእምነቱ፤
አገር ምድሩ አነባ - ማንም አልቀረም ቤቱ
ለህዝብ መኖር ያስከብራል - ጥልቅ ፍቅር ነው ውጤቱ፤
ውሽንፍር ጐርፍ ሳያግደው - ወገን በሲቃ ተውጦ
በመሪው ያደረ ተስፋው - ድንገት እንደ ሰም ቀልጦ
መቼም አይበረክትም - ትውልድ አገርን ገንቢ
ቅርብ አዳሪ ነው አሉ - ወትሮም ሩቅ አሣቢ፣
ቀብሩ ለምን ታወጀ - ጀግና ምን ቀብር አለው
ማረፊያው የህዝቦቹ ልብ - ሃውልቱም ህያው ሥራው ነው፡፡
የአገሬ ኢትዮጵያ ማህፀን - ሚሊዮን ይውለድ የእማማ
ችግር ጉልበቱ ይራድ - መለስ ያንተን ስም ሲሰማ
ድህነት ታሪክ ይሆናል - ብለሃል አንተም ታይቶሃል
በብልፅግና ህዳሴ - ታሪክህ በወርቅ ይፃፋል፡፡