Monday, 21 June 2021 00:00

የዘንድሮው ሐጂ ለዜጎችና ለነዋሪዎች ብቻ እንደሚፈቀድ ሳዑዲ አስታውቃለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የሳዑዲ አረቢያ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ከኮሮና ስጋት ጋር በተያያዘ ለ1442ኛ ጊዜ በሚካሄደው የዘንድሮው የሐጅ ስርዓት ላይ መሳተፍ የሚችሉት በአገሪቱ የሚገኙ ዜጎችና በነዋሪነት የተመዘገቡ ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ከሰሞኑ አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ በሳምንቱ መጀመሪያ ባወጣው መግለጫ እንዳለው፣ በዘንድሮው ሐጅ ስነስርዓት ለመሳተፍ የሚችሉት 60 ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ ሲሆኑ፣ ስር የሰደደ በሽታ የሌለባቸው፣ የኮሮና ክትባት የወሰዱ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 65 አመት ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡


Read 4010 times