Saturday, 19 June 2021 16:36

“በትግራይ 33 ሺህ ህፃናት በረሃብ ሳቢያ በሞት አፋፍ ላይ ይገኛሉ” ዩኒሴፍ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 በትግራይ 33 ሺህ ያህል ህፃናት በረሃብ ሳቢያ  በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ ያመለከተው የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ)፤ እኒህ ህጻናት አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው በሪፖርቱ አሳስቧል፡፡
በአጠቃላይ በትግራይ ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ 2.2 ሚሊዮን ዜጎች የረሃብ አደጋ እንደተጋረጠባቸውና ከእነዚህ ውስጥ 140 ሺህ ያህሉ ከወዲሁ ለረሃብ መጋለጣቸውን ሪፖርቱ   ጠቁሟል፡፡
በረሃብ አደጋ ውስጥ ከሚገኙት 33 ሺህ ያህሉ ህፃናት መሆናቸውን ያመለከተው ሪፖርቱ፤ ህፃናቱ በህይወትና በሞት መካከል የሚገኙና አፋጣኝ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ናቸው ብሏል፡፡
በረሃብ ውስጥ ከሚገኙት ህፃናት በተጨማሪ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 65 ሺህ ያህል ህፃናት አስቸኳይ አልሚ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸውም  የተቋሙ ሪፖርት ይጠቁማል፡፡
የህፃናቱን ህይወት ለመታደግ  ጥረት እያደረገ መሆኑን ያስታወቀው ዩኒሴፍ፤ ሌሎች ለጋሽ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉም ጥሪውን አቅርቧል፡፡በሌላ ሪፖርት፣ በትግራይ ለምግብ እርዳታ ከተጋለጡ 5.2 ሚሊዮን ዜጎች መካከል  3.3 ሚሊዮን ያህሉ ድጋፍ እያገኙ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፎች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አመልክቷል፡፡


Read 912 times