Sunday, 13 June 2021 20:03

የስነተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

 የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትና የስነ ተዋልዶ ጤናን የተሳሰረ የሚያደርገው ነገር አለ፡፡ የስነተዋልዶ ጤና ሲባል የእናት ጡትን ጨምሮ በአጠቃላይ ማህጸንን እና ከማህጸን ጋር ተያያዥ የሆነውን አካል የሚመለከት ሲሆን የቤተስብ ምጣኔ ግን ምን ያህል ልጅ በምን ያህል ጊዜ የሚለውን አቅምን ባገናዘበ መንገድ ማቀድን የሚመለከት ነው፡፡ ይህ አገልግሎት ትክክለ ኛውን መንገድ ይዞ ካልተተገበረ ጉዳት ማስከተሉ እውን ነው፡፡ ለምሳሌም ከእቅድ በላይ እርግዝናን ተከትሎ በሚመጣው ደህንነቱ በተጠበቀም ይሁን ደህንነቱ በላተጠበቀ መንገድ ጽን ስን የማቋረጥ ድርጊት የተለያዩ ጉዳቶች ሊያስትል ይችላል፡፡ ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል ሲባል የሚወሰዱ የተለ ያዩ መከላከያዎች በተለያየ ምክንያት ለሚወስዱአቸው እናቶች ባይስ ማሙ እና መስተካከል የሚገባው ነገር ቢኖር ትክክለኛውን ባለሙያ ማግኘት ግድ ይላል። በስነተዋልዶ ጤና እና በቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ዙሪያ የእናቶችን እና የጨቅላ ህጻናቱን ጤንነት እና ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር ለመጀመሪያ ጊዜ በሙያው የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ኢትዮጵያ አግኝታለች፡፡
ባለፈው እትም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠውን የስነተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ ምጣኔ ንኡስ እስፔሻላይዜሽን (Sub Specialty) የትምህርት ምንነትና የስራ ባህርይ ከመጀ መሪያዎቹ ሶስት ምሩቆች አንዱ የሆኑትን ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳን አነጋግረን ለንባብ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡
የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት በስነተዋልዶ ጤና ዘርፍ የሚፈረጅ እና በርካታ ክትትሎች እና የምክር አገልግሎት የሚያስፈልገው መሆኑ እሙን ነው፡፡ በዚህ ረገድ የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲበረታቱና በአለም አቀፍ ደረጃ ለእይታ ወይንም ለንባብ እንዲቀርቡ የሚያስችሉ ህትመቶች እና ድረገጾች እውን መሆናቸውን ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ አብራርተዋል። የስነተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ ምጣኔ ንኡስ እስፔሻላይዜሽን በአለምአቀፍ ደረጃ በተለይም ባደጉት አገራት የቆየ ቢሆንም በአፍሪካ ግን ኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ነች፡፡ በኢትዮጵያም ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰለጠኑት የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስቶች መካከል ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ አንዱ ናቸው፡፡  ዶ/ር ተስፋዬ በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያም አለም አቀፍ ልምዶችን መቅሰም እና ማካፈል የመሳሰሉትን ተግባራዊ በማድረግ በኢትዮጵያ አገልግሎቱን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች በስፋት እየተሰሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
ለዚህ እትም ካነሳናቸው ነጥቦች መካከል ይህ የስነተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ ምጣኔ ልዩ ትምህርት ከመሰጠቱ በፊት ትግበራው ምን ይመስል ነበር የሚለው ይገኝበታል፡፡ ዶ/ር ተስፋዬ ሲመልሱ ከዚህ በፊት በነበረው ኤክስፐርትና ባለሙያው ባለው አቅም በጣም ጥሩ ስራ ይሰራ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ስልጠና በመምጣቱ እና ባለሙያዎችን በተገቢው መንገድ በማሰልጠኑ የነበረውን ስራ ለማገዝ እጅግ ይረዳል። አለምአቀፍ እይታን ማለትም አለም በምን መልኩ ይሰራል የሚለውን እይታ ይዘው የመጡ ባለሙያዎች ወይንም በስነተዋልዶ ጤና የሚገባውን ያህል ትልቅ እውቀት ይዘው የመጡ ባለሙያዎችን ወደ አመራሩ ማምጣት ይፈለጋል፡፡ ያንን ማምጣት አሁን ለሚሰራው የስነተዋልዶ ጤና ስራ ተጨማሪ ግብአት ይሆነዋል የሚል እምነት አለን፡፡ በተለይም እንደኢትዮጵያ አይነት ተመሳሳይ አቅም ያላቸው እንደ ኔፓል ያሉ ሀገራት ከየት ተነስተው ወዴት ደረሱ የሚለውን ስንመለከት ልምዳቸውን በመቅሰም ጥሩውን ወይንም በጎውን በመውሰድ ወደሀገር ውስጥ በማምጣት ለምንሰራው ስራ ትልቅ ግብአት ይሆናል ብለዋል ፡፡
የምርምር ስራዎች በኢትዮጵያ ገና አልተሰሩም ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህ የህንን የቤተሰብ ምጣኔ እና የስነተዋልዶ ጤና በሚመለከት የምርምር ስራዎች በብዛትና በጥራት እንዲሰሩ እነዚህ በዘርፉ እስፔሻሊስት የሆኑት ግለሰቦች ባለሙያዎችን ማበረታታት እና የተሻለ ፖሊሲን ለመቅረጽ እና የተሻለ አሰራርን ለመከተል የተሻለ መንገድን ለመቅረጽ ያስችላል የሚል እምነት አለን ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት ስራዎች ከአሁን ቀደም በሐኪሞች ብቻ ሳይሆን በነርሶችም ጭምር የሚሰሩ ናቸው። ነገር ግን የስነተዋልዶ ጤና ንኡስ እስፔሻሊስቶች ድርሻ አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡ በቤተሰብ ምጣኔ ይደረስበታል ተብሎ የታቀደው Sustainable Development Goal የገመተው የወደፊት ውጤት የሚገልጸውን እውን ለማድረግ የተቻለውን ያህል ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ኢትዮጵያ አሁን በቤተሰብ ምጣኔ ከ41-42% ብትደርስም ከ20% በላይ ጥንዶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን እየፈለጉ ያላገኙ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህም አገልግሎቱን ሁሉም ጋ ተደራሽ የማድረግ እንዲሁም ከህክምናው አገልግሎት አንጻር የዳበረ እውቀትን መያዝ ያስፈልጋል፡፡ እንዲሁም ጥራት ያለው የምክር አገልግሎትን ማድረስ የሚለው አንዱ ትልቁ ስራ ነው። በዚህም ህብረተሰቡን በምን መንገድ ማግኘት እና በምን ዘዴ ማማከር ይገባል? እንዴት ነው ጥቅሙን እና አገልግሎቱን ማስረዳት የሚቻለው? የሚለውን እንዲሁም በምን መልክ ወደሚፈለገው ግብ መድረስ ያስፈልጋል የሚለውን ከጥናትና ምርምር ውጤቶች እውነታ በመነሳት መስራት ይጠበቃል፡፡
የህምናው ጥበብ ብዙ ነገሮች የሚስተዋሉበት እና ጥንቃቄንና ትእግስትን የሚፈልግ አገልግሎት ነው። ለምሳሌ ከወር አበባ ኡደት መዛባት ጋር ሊገናኝ ይችላል፡፡ የወር አበባ መዛባት ከምክን ያቱ ጀምሮ ያለበትን ባህርይ እና ያደረሰው የማህጸን የጤና ችግር መኖር አለመኖሩን መፈተሽ በራሱ ከስነተዋልዶ ጤና ጋር ስለሚያያዝ አንዱ የስራው ዘርፍ ነው፡፡
የስነተዋልዶ ጤናና የቤተሰብ ምጣኔ ንኡስ እስፔሻላይዜሽን (Sub Specialty) አስቀድሞውኑም ትምህርቱ የሚሰጠው የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት ለሆኑት ባለሙያዎች በመሆኑ ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም ችግሮች አስቀድሞውኑም የታወቁ በመሆናቸው ችሎታን አዳብሮ በተሻለ መንገድ አገልግለቱን ለመስጠት እንዲቻል ዝግጁ የሚያደርግ ነው፡፡ በትምህርቱ የሚካ ተቱት የስነተዋልዶ ጤናና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን የሚመለከቱ የህክምና አገልግሎቶች በጣም በርካታ ናቸው፡፡
ትልቁ ገጽታ እንደሀገር የእናቶችን ሞት መቀነስ ነው፡፡ አሁን ባለው መረጃ መሰረት ከ100.000 በሕይወት ከሚወልዱ እናቶች 401/አካባቢ ይሞታሉ። በእርግጥ ይህ ከታሰበው ግብ ወደሁዋላ ወይንም ከታሰበው እቅድ ያልተደረሰ መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ይህንን የስነተዋልዶ ጤናና የቤተሰብ ምጣኔ እስፔሻላይዝድ ያደረጉ እና በስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያ ዎች የታሰበውን ከማሳካት አንጻር ብዙ ይጠበቅቫቸዋል፡፡
የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ብዙ ዘዴዎች አሉ። ከእነዚህ ዘዴዎች ውስጥ ኢትዮጵያ ገና ታዳጊ አገር እንደመሆንዋ ብዙ ወጪ ሳይኖር የእናቶች ሞትን መቀነስ የሚቻልባቸውን መንገዶች መመልከት አንዱ አላማ ነው፡፡ የአለም የጤና ድርጅት ባወጣው እቅድ ለመመራት ጥናትና ምርምሮችን በስፋት እና በጥራት እንዲሰሩ በማድረግ እና ተገቢ የሆኑ ፖሊሲዎችን በመቅረጽ የእናቶችን ሞት መቀነስ ዋናው የትምህርቱ ግብ ነው፡፡
ሌላው ነገር የጥናትና ምርምሩ ሂደት ነው፡፡ ይህ ስራ ስልጠናውን ለወሰዱት ብቻ ሳይሆን ሌሎቹም ባለሙያዎች በምን መልክ ጠቃሚ የሆኑ የምርምር ውጤቶችን ያወጣሉ የሚለውን መመልከት እና ባገኘነው ልምድና እውቀት መምራት መቻልም ይጠበቅብናል፡፡ ለዚህም ምርምሮች እንዴት ይሰራሉ የሚለውን ማሰልጠን ይጠበቅብናል፡፡ ይህ እውን ከሆነ በስፋትና በጥራት በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ምርምሮችን በአለም አቀፍ ደረጃ መቀባበል ስለሚ ያስችል ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ፡፡
ባጠቃላይም በትምህርቱ ምክንያት በተዘረጋው ግንኙነት በተለያዩ ሀገራት እንደነ አሜሪካ ባሉት ማለት ነው የስነተዋልዶ ጤና ህክምና አገልግሎት እንዴት እንደሚሰጥ ያየን ሲሆን ያንን ለኢ ትዮጵያ እናቶች ለመተግበር ፍላጎት አለ፡፡ በኢትዮጵያ እናቶች የስነተዋልዶ ጤና አገል ግሎት እንዲያገኙ፤ ለስነተዋልዶ ጤና የተመቸ ፖሊሲ እንዲኖር ለማድረግ ጥረት ማድረግ እና የሴ ቶችን ችግር ተረድቶ ንቁ የሆነ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችል የሰው ኃይልም ወደፊት እንዲኖር ለማድረግ በእቅድ ተይዞአል፡፡ በስልጠናው ከተመረቁት ሶስት ባለሙያዎች በተጨማሪም ስል ጠናውን በመውሰድ ላይ ያሉ ሌሎች ባለሙያዎች መኖራቸውን ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ ገልጸዋል፡፡     

Read 10763 times