Sunday, 13 June 2021 19:36

"በትግራይ 350 ሺ ሰዎች ለረሃብ ተዳርገዋል የሚለው መረጃ ሃሰተኛ ነው” - መንግስት

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

  “በርካታ የትግራይ አካባቢዎች በረሃብ ዋዜማ ላይ ይገኛሉ” - የተመድ ዋና ፀሃፊ ኦንቶኒዮ ጉቴሬዝ
                                
               በትግራይ ክልል 350 ሺ ሰዎች ለረሃብ ተዳርገዋል ተብሎ  በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የሚሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ ነው ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ሲሆን፤ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው፤ በርካታ የትግራይ አካባቢዎች በረሃብ ዋዜማ ላይ ይገኛሉ ሲሉ በቲውተር ገፃቸው አስጠንቅቀዋል፡፡
ቀደም ሲል የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ 5.2 ሚሊዮን ዜጎች በትግራይ ክልል አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል የሚል ሪፖርት ማውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን መንግስት ከእነዚህ ውስጥ ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የምግብ እርዳታውን ተደራሽ ማድረጉን አመልክቷል።
የተለያዩ አለማቀፋዊ መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው፤ በትግራይ ከ350 ሺ በላይ ዜጎች ለረሃብ ተዳርገዋል መዘገባቸውን የጠቆሙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ምላሽ፤ መረጃው ሃሰተኛ ነው፤ ረሃብ አልተከሰተም፤ መንግስት የተቻለውን እርዳታ ሁሉ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
ከቃል አቀባዩ መግለጫ ቀደም ብሎ በትዊተር ገፃቸው ትግራይን በተመለከተ መልዕክት ያስተላለፉት የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ በትግራይ በርካታ አካባቢዎች የረሃብ አደጋ አንዣብቧል- ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በትግራይ ጉዳይ በየቀኑ የሚወሰዱ እርምጃዎች የሰዎችን ነፍስ በህይወት የማቆየት አይነት ሊሆን ይገባዋል ያሉት ዋና ፀሃፊው፤ መንግስት ሰብአዊ ድጋፎች ወደ ትግራይ  የሚደርስበትን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ማመቻቸት አለበት-ብለዋል፡፡

Read 715 times