Sunday, 13 June 2021 19:34

ም/ቤቱ የ26 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጸደቀ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

ከውጭ የሚገኘው ድጋፍ በመቀነሱ ምክንያት ለሚከሰቱ  የኢኮኖሚ  ችግሮች  መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችልና  በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከተወሰደው ህግን የማስከበር  ዘመቻ ጋር በተያያዘ የተከሰቱ ተጨማሪ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚያግዝ እንዲሁም በመጪው ክረምት ሊከሰት ይችላል ተብሎ የታሠበውን  የጎርፍ አደጋ  ለመከላከል ተግባር ይውላል የተባለውን የ26 ቢሊዮን ብር  ተጨማሪ በጀት  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ሰሞኑን አጸደቀ ።
ምክር ቤቱ ከትናንት በስቲያ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን ተጨማሪ በጀትና የወጭ አሸፋፈን ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ በሃገር ውስጥ ባንክ ብደር የሚሸፈን 26 ቢሊዮን ብር የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ረቂቅ አዋጅን ያጸደቀ ሲሆን፣ ተጨማሪ በጀቱ የዋጋ ግሽበቱን እንዳያባብሰው በጥንቃቄ መሰራቱ ተገልጿል።  በጀቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተሰራው የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መሰረት ኢኮኖሚው ካመነጨው ገንዘብ ይሟላል ተብሏል።

Read 725 times