Print this page
Saturday, 12 June 2021 00:00

የዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ ነገ ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በዘንድሮው አገራዊ ምርጫ በግል እጩነት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምርጫ ክልል 28 የሚወዳደረው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያውን ነገ በሲኤምሲ አደባባይ  ያካሂዳል፡፡
ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ በሚጠበቀው በዚህ የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ የተለያዩ ኪነ- ጥበባዊ ዝግጅቶች የሚቀርቡ ሲሆን የብሔራዊ ቲያትር የሙዚቃ ባንድ ዝግጅቱን ያደምቀዋል ተብሏል፡፡
የምርጫ ቅስቀሳው የማጠቃለያ ፕሮግራም ከተለመደው በተለየ አዝናኝ እንዲሁም የምርጫ ክልሉን  ነዋሪና መራጭ ህብረተሰብ የሚያሳትፍ እንደሚሆን የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ለአዲስ አደማስ ተናግረዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ኬሚካል ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎችና በምርጫ ክልሉ ነዋሪ የሆኑት ተሰሚነት  ያላቸው ሰዎች ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል፡፡ ዲያቆን ዳንኤልም ክብረት ቁምነገር አዘል የሆኑ መልዕክቶቹን  በዚህ መድረክ ላይ እንደሚያስተላልፍ አዘጋጆቹ ጠቁመዋል፡፡
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በምርጫ ክልል 28 በየካ ክፍለ ከተማና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2,3,4,5 እና 10፣ በ151 ምርጫ ጣቢያዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በግሉ እንደሚወዳደር ይታወቃል፡፡


Read 971 times
Administrator

Latest from Administrator