Sunday, 13 June 2021 00:00

“ሀገር ምን ትሻለች3” ኪነ-ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በየወሩ የሚካሄደው እና በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት የሚከወነው የዚህ ወር መሰናዶ “ሀገር ምን ትሻለች” በሚል መርህ የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዕለቱም ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ መምህር ፋንታሁን ዋቄ፣ መምህር አገኘሁ አዳነ፣ ደራሲ መሃመድ አሊ ቡርሃንና  መምህር መስፍን ሰለሞን ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን፣ አርቲስት ሱራፌል ተካና አርቲስት ካሌብ ዋለልኝ ወግ፣ ገጣሚያኑ ሰለሞን ሳህለ ትዕዛዙና ገጣሚ ተስፋሁን ከበደ (ፍራሽ አዳሽ) ግጥም እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡ በሻሎም ለኢትዮጵያ ሙዚቃ የሚታጀበው የኪነ- ጥበብ ምሽቱ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር እንደሆነም ታውቋል፡፡

Read 10875 times