Saturday, 12 June 2021 12:43

“የኮከቡ ሰው” ቴአትር ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በዓለሙ ገብረአብ ተተርጉሞ በዳግማዊ አመለ ወርቅ ፈይሳ የተዘጋጀውና በተዋናይት መስከረም አበራ ፕሮዲዩስ የተደረገው “የኮከቡ ሰው” ቴአትር ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡
የኮሜዲ ዘውግ ያለው ቴአትሩ በደራሲ ካርል ዊትሊንገር ተደርሶ አዛማጅ ትርጉሙ በአንጋፋው አርቲስትና ከዓመታት በፊት በሞት ባጣነው ዓለሙ ገብረአብ መሰራቱ ታውቋል፡፡
ፕሮዲዩሰሯ መስከረም አበራ፣ አማኑኤል ሀብታሙ፣ፍቃዱ ከበደና እንዳለ ብርሃኑ በሚተውኑበት በዚህ ቴአተር ምረቃ ላይ በርካታ የኪነ-ጥበብ ሰዎች፣ የጥበብ አፍቃሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚታደሙ ሲሆን ከምረቃው በኋላም ዘወትር ሀሙስ በ11፡00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንዲሁም ዘወትር ማክሰኞ በ11፡00 በኤድና ሞል ሲኒማ በቋሚነት ለእይታ እንደሚበቃ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡


Read 1675 times