Saturday, 05 June 2021 12:44

የስነተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ ምጣኔ እስፔሻሊስትነት፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

   የቤተሰብ ምጣኔ እና የስነተዋልዶ ምጣኔ Sub Specialist በንኡስ ማእረግ ትምህርቱ በሀገ ራችን ሲሰጥ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲሆን በአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛው ነው፡፡ በቤተሰብ ምጣኔ እና በስነተዋልዶ ጤና Sub Specialist (ንኡስ እስፔሻሊስትነት) በኢትዮጵያ ለመጀ መሪያ ጊዜ ከሰለጠኑት ሶስት ባለሙ ያዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ ቀድሞውኑም የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔ ሻሊስት የነበሩ ሲሆን አሁን በተጨማሪ የቤተሰብ ምጣኔ እና የስነተ ዋልዶ ጤና Sub Specialist (ንኡስ እስፔሻሊስት) ለመባል በቅተዋል፡፡
የቤተሰብ ምጣኔ እና የስነተዋልዶ ጤና ንኡስ እስፔሻሊስትነት በአደጉት አገራት አሜሪካን እና ካናዳን ጨምሮ ብዙ አመታትን ያስቆጠረ ፕሮግራም ነው፡፡ በአፍሪካ ግን ጋና ብቻ ሙያውን የተቀላቀለች ስትሆን ኢትዮጵያ ሁለተኛዋ አገር ናት፡፡ ትምህርቱ ሁለት አመት ተኩል ጊዜን ይፈልጋል፡፡ የስነተዋልዶ ጤና ንኡስ እስፔሻሊስትነት በውስጡ ብዙ የያዛቸው ጥቅሎች አሉ። በስነተዋልዶ ጤና ላይ ከዚህ በፊት በማስተርስ ዲግሪ ፕሮግራም የሚሰጡ ትምህርቶቹ ቢኖሩም ይህ ግን ከዚያ ለየት ይላል ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ፡፡
የስነተዋልዶ ጤና Sub Specialist በሚለው ፕሮግራም ውስጥ ለመግባት በመጀመሪያ የማህ ጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት መሆን ያስፈልጋል፡፡ ትምህርቱ በውስጡ የተለያዩ ንኡስ አካላት አሉት፡፡ ለምሳሌም፡-
በምርምር ደረጃ ሰፊ የሆነ ድርሻ አለው፡፡ በዚህም ከሌሎች ንኡስ እስፔሻሊስትነቶች የተለየ ችሎታ ወይም Skill ያጎናጽፋል፡፡  
ከሌላው ንኡስ እስፔሻሊስትነት በተለየ ሰፊ የሆነ አለም አቀፍ እይታ አለው፡፡
ፖሊሲ ላይ ሰፊ የሆነ እይታ ወይንም እንቅስቃሴዎች አሉት፡፡  
ስለዚህም በሁለቱ አመት ተኩል ጊዜ ውስጥ አንዱ አመት የ Skill ወይም እውቀትን የማጎ ልበቻ አመት ሲሆን ስልጠናውን የሚከታተለው ሰው ባለበት ሆስፒታል ውስጥ ከውጭና በአገር ውስጥ ካሉ አስተማሪች ጋር አብረው ችሎታን የሚያዳብሩበት ፕሮግራም ነው። ይህም የስል ጠናው እድል ባለበት ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ ተተግብሮአል፡፡
ሁለተኛው አመት ደግሞ ምርምርና ፖሊሲዎች ላይ ያሉ ነገሮች የሚሰሩበት ነው፡፡ የህብረ ተሰብ ጤና (Public Health) የሚማርበት እንዲሁም የአለም የጤና ድርጅት የአንድ አመት attachment ወይንም ተጨማሪ ልምድ የሚገኝበት ፕሮግራም አለው ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ፡፡
የቤተሰብ ምጣኔ እና የስነተዋልዶ ጤና ንኡስ እስፔሻሊስት ማለት ምን የስራ ድርሻ አለው ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ ዶ/ር ተስፋዬ የሚከተለውን መልስ ነበር የሰጡን፡፡
በጥናትና ምርምር ደረጃ ያለው ሁኔታ ሲታይ በአስርና አሰራ አምስት አመታት ውስጥ በስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ ብዙ ለውጦች እንዳሉ እና እድገቶች እንደተመዘገቡ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኛውን ጊዜ ለስራ መመሪያነት ወይም ለመረጃ የምንጠቀምባቸው ከውጭ የሚገኙ የጥናትና የምርምር ውጤቶች ናቸው። በአገር ውስጥ በበቂ ሁኔታ በጥናትና ምርምር የሚሰራ ኤክስፐርት የለንም ወይንም ጥናትና ምርምሮቹም ሲታዩ በቂ አይደሉም፡፡ ስለዚህ በዚህ ፕሮግራም የሰለጠኑ ባለሙያዎች አንዱ ድርሻቸው በአገር ውስጥ በባለሙያዎች የሚሰሩ ጥራታቸውን የጠበቁ የምርምርና የጥናት ውጤቶችን ማውጣት ነው፡፡
በኢትዮጵያ የተሰሩ ጥራታቸውን የጠበቁ የጥናትና ምርምር ውጤቶች ሲኖሩ የሚወጡት ፖሊ ሲዎችና መመሪያዎች በአገር ውስጥ የተሰሩ ስለሚሆን ለወደፊት እድገት እና ለሚታሰበው ግብ ጥሩ የሆነ አስተዋኦ ይኖረዋል፡፡ ስለዚህም በስነተዋልዶ ጤና ንኡስ እስፔሻሊስትነት የሚሰለጥ ኑት ባለሙያዎች በጥናትና ምርምር ዙሪያ በቂ የሆኑ ባለሙያዎችን ማፍራት አንዱ የስራ ድርሻ ቸው ነው፡፡
ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ በተጨማሪ እንዳብራሩት የስነተዋልዶ ጤና ንኡስ እስፔሻሊስትነት የጥና ትና ምርምር ውጤትን ጥራትና ብዛት በመጨ መሩ ረገድ ከፍተኛ የስራ ድርሻ ያለው ሙያ ስለሆነ በሁለት አመት ተኩል ጊዜ በስነተዋልዶ ጤና ንኡስ እስፔሻሊስትነት የተመረቅነው ሶስት እስፔሻሊስቶች አብረውን ከሚሰሩ ሐኪሞች ጋር በመሆን  እስ ከአሁን ድረስ ከሰላሳ በላይ የሆኑ በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ያተኮሩ የጥናትና ምርምር ውጤቶች በአገር ውስጥና በአለም አቀፍ ጆርናሎች  ለሕት መት እንዲበቁ በማድረጋችን ለአለም ህዝብ ይፋ ሆነዋል፡፡ እንዲሁም በኦንላይን መረጃውን የሚፈልግ ሁሉ በhttps://www.spirhr.org/ category/staff/ አድራሻ ማግኘት ይችላል ብለዋል፡፡
ሌላው የቤተሰብ ምጣኔ እና የስነተዋልዶ ጤና ንኡስ እስፔሻሊሰትነት የሚኖረው ድርሻ (clinical skill) በህክምናው ላይ ያተኮረ ሙያ ነው፡፡ ለምሳሌም፡-
የቤተሰብ ምጣኔ ተጠቃሚ ቁጥር ቀደም ሲል ከ10% በታች የነበረ ሲሆን አሁን ግን ከ40% በላይ ደርሶአል፡፡
ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስን የማቋረጥ ተግባር ቀደም ሲል በሰፊው ይስተዋል የነበረ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞም የእናቶች ሞት ቁጥር በርካታ ነበር፡፡ አሁን ግን በፖሊሲና በአገር ደረጃ በተሰሩ ስራዎች ጽንስን ማቋረጥ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እንዲሆን ሁኔታዎች በመመቻቸታቸው ቁጥሩ በጣም ቀንሶአል፡፡
ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስን የማቋረጥ ተግባር ጋር ወይንም የቤተሰብ ምጣኔ ቁጥር ከመ ጨመር ጋር ተያይዞ የሚመጡ የጎንዮሽ ችግሮች አሉ። እነዚህን የጎንዮሽ ችግሮች ለማ ስወገድ በጠቅላ ላው ሕክምና አገልግሎት ሊሰጡ የማይችሉ ከሆነ በስነተዋልዶ ጤና ንኡስ እስፔሻሊስቶች ይሰጣል፡
የወንድ የዘር ፍሬ ማስቋጠር፤ የሴት ቱቦን መቋጠር፤ የመሳሰሉትን ስራዎች መስራት ብቻም ሳይሆን ለሌላውም በስልጠና መስጠትን በስፋት የምንሰራው ስራ ሲሆን ወደፊትም የሚቀጥል ነው ብለዋል፡፡
የቤተሰብ ምጣኔ ሲነሳ ብዙውን ጊዜ ለሴትዋ የተተወ ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ነገር ግን የወንዶችም ጉዳይ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ የወንድ የዘር ፍሬ ማስቋጠር በሌላው የአለም ክፍል በስፋት የሚሰራ ሲሆን በእኛ አገር ግን ከመቶ አንድ በሚባል ደረጃ ስለሆነ በስፋት አይስተዋልም፡፡ ሴቶች በተለያዩ ምክንያቶች ወይንም የጤና ጉድለቶች የተነሳ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት መውሰድ እንደማይችሉ የታወቀ ሲሆን ወንዶች ድርሻቸውን ለመወጣት ፈቃደኛ ቢሆኑ ይመከራል። አንዳንድ ጊዜ ወንዶች ባለቤታቸው ልጅ በመውለድ እና በመሳሰሉት በቀዶ ሕክምናም ይሁን በሌሎች ምክን ያቶች ሰውነትዋ የደከመ በመሆኑ ከእስዋ ይልቅ እኔ መከላ ከያውን ማድረግ እመርጣለሁ ብለው ወደህክምናው የሚቀርቡ አሉ፡፡
የወንድ የዘር ፍሬን ማስቋጠር በጣም ቀላልና አስር ደቂቃ የማይፈጅ ደህንነቱ አስተማማኝ የሆነ አገልግሎት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ በስፋት ሊሰራበት የሚገባ በመሆኑ የቤተሰብ ምጣኔና የስነተዋልዶ ጤና ንኡስ እስፔሻሊስትነት በዚህ ላይ በስፋት እንድንሰራ ሙያው ያስገድደናል እኛም ዝግጁ ነን ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ።
ሙያው የአለም አቀፍ እይታንም የመጨመር የራሱ የሆነ ሰፊ አስተዋጽኦ አለው፡፡ እስፔሻ ሊስቶቹ ለአንድ አመት የአለም አቀፍ ልምድ ሲቀስሙ እያንዳንዱ ባለሙያ ለአለም አቀፉ የጤና ድርጅት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የስራ ግንኙነት እንደሚኖረው እና በዚህም ስለሀገር ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ምን አይነት ፖሲዎች እንዳሉ፤በታዳጊ ሀገራት እና ባደጉት ሀገራት ምን አይነት ፖሊሲዎች እንዳሉ፤የተለያዩ ሀገራት ቀደም ሲል የነበሩ ፖሊሲዎቻቸውን በምን ተኩ፤ የተተኩ ፖሊሲዎች ምን ጥቅም አላቸው የሚለውንና  ከተለያዩ ሀገራት ልምድን በመቅሰም በስነተዋልዶ ጤና ላይ ከምን ተነስተው ከምን ደረሱ የሚለውን እይታ የምንወስድ ሲሆን ይህ አሰራር ወደሀገራችን ስንመለስ ለምንሰራው ስራ ግብአት ይኖረዋል፡፡ ስለዚህም በሀገር ውስጥ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ልምድ በመቅሰም በሀገር ውስጥ በቤተሰብ ምጣኔ እና በስነተዋልዶ ጤና ላይ የሚሰሩ ስራዎችን ለማጎልበት ይረዳል ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ የቤተሰብ ምጣኔ እና የስነተዋልዶ ጤና Sub Sepeshalist (ንኡስ እስፔሻሊስት)፡፡

Read 13806 times