Print this page
Saturday, 05 June 2021 12:30

በኦሮሚያ ክልል 31.7ቢ.ብር ወጪ የተደረገባቸው 11 ሺህ ፕሮጀክቶች ይመረቃሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

     የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት ተደምረው ሲካሄዱ የቆዩና የተጠናቀቁ 11 ሺህ  የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በአንድ ሳምንት መርሃ ግብር ውስጥ እንደሚያስመርቅ ተገለፀ፡፡
በኦሮሚያ የተሰራው የተቀናጀ ውጤታማ ስራ ነው ያሉት አቶ ሽመልስ፤ የእነዚህ ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ መጠናቀቅ ቁርጠኛ አመራር ካለ የመፈፀም አቅማችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠቀም እንደሚቻልና የሃገሪቱ የመልማት አቅም ከፍተኛ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል፡፡
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች የተገነቡትና የሚመረቁት 11 ሺ ፕሮጀክቶች 31.7 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል ተብሏል፡፡
በክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ተጀምረው ከተከናወኑ ፕሮጀክቶች መካከል ኢፋ ቦሩ (የነገ ብርሃን) በሚል ስያሜ በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተገነቡ ከ70 በላይ ደረጃቸውን የጠበቁ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ይገኙበታል ብለዋል- አቶ ሽመልስ በመግለጫቸው፡፡
በአንድ ሳምንት ወይም በ10 ቀናት ዘመቻ ከሚመረቁ 11 ሺህ ፕሮጀክቶች መካከል የጤና ኬላዎች፣ ሆስፒታሎች፣ መንገዶች ፣ ት/ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም  በሱሉልታ የተገነባውና በአትሌት ደራርቱ ቱሉ የተሰየመው የስፖርት አካዳሚና ማዕከልን  ይጨምራል፡፡
በየከተሞቹ የተገነቡ የፍትህ ተቋማትና አስተዳደር ህንፃዎች እንዲሁም የቦረና ዩኒቨርስቲን የሚያካትት በክልሉ ትላልቅ ከተሞች በአማካይ ከ40 እስከ 50 የሚደርሱ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ይመረቃሉ፡፡ የፕሮጀክቱ ምርቃት ከግንቦት 25- ሰኔ 5 የሚዘልቅ ነው ተብሏል፡፡


Read 13452 times