Saturday, 29 May 2021 14:43

የቪዛ ክልከላ መዘዞች!

Written by  ውብሸት ሙላት
Rate this item
(0 votes)

     የቪዛ ክልከላ ከሚያስከትላቸው መዘዞች ዋናው እልህ መጋባት ነው። በእልህ መጋባት ሰለባ የሚሆነው ሕዝብ ነው። የኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ ክልከላ መደረጉ በዋናነት የጎዳው የኤርትራን ሕዝብ እንጂ ባለሥልጣናቱን አይደለም። የተለያዩ ማዕቀቦች ኤርትራ ላይ በመጣሉ በቀጥታ ተጎጂ የሆነው ሕዝቡ ነው። በኢኮኖሚ ተጎዱ። በሰብአዊ መብት አያያዝ ተጎዱ። ዴሞክራሲን ለማስፈንም አልጠቀማቸውም። ፕሬዚዳንት ኢሳይያስና አስተዳደሩ እልህ መጋባታቸው ቀጠለ።
ኤርትራ ላይ ተጥሎ ከቆየው የተለያየ ማዕቀብ ጀርባ ትሕነግና ሱዛን ራይስ ነበሩ። ሱዛን ራይስ ወደ ዲፕሎማሲው መንደር በተቀላቀለችበት ሰሞን ገና በወጣትነቷ ከኢሳይያስ ጋር ተላተመች። ኢሳይያስም ያኔ “You are by the book diplomat” አላት አሉ። ‘እሷም እንዴት የወረቀት፣ የመጽሐፍ ብቻ ዲፕሎማት ይለኛል? ነባራዊውን ዓለማ አቀፍ የዲፕሎማቲክ አተካራ አታውቂም አለኝ?’ በሚልም ግላዊ ስሜት ያደረባት እስኪመስል ድረስ እና ኢሳይያስን ለመበቀል ከመለስ ዜናዊ  ጋር ተለጥፋ፣ ‘’ቤተሰብ’’ም ሆና የኢሳይያስ አስተዳደርን ተበቀለች።
ኢሳይያስ ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ መላላት፣ የወዳጇ የትሕነግ ሞት የውሽማ ሞት የሆነባት ይመስላል። ሱዛን ራይስ ለብሊንከን አለቃው ነበረች። አሁን ደግሞ እሱ አለቃዋ ሆኗል። በሱዛን ራይስ ምክርም ይሁን ጫና ወይም በሌላ ምክንያት፣ ኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረውን ዓይነት ማዕቀብ (ክልከላ) ኢትዮጵያም ላይ መጣል ጀምረዋል።
አሳዛኙ ነገር፣ እንዲህ ዓይነት ክልከላ ወይም ማዕቀብ የትግራይ ሕዝብን ሁኔታ ለማሻሻል አስተዋጽኦ የማይኖረው መኾኑ ነው። እንደውም በእልህም በእርዳታና ድጋፍ ማነስም የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ  ቀውስ (Humanitarian Crises) እንዳያባብሰው ነው።

Read 2119 times