Saturday, 29 May 2021 14:40

አስሩ አሜሪካን የማንበርከኪያ ዘዴዎች

Written by  ፋሲል የኔአለም
Rate this item
(0 votes)

 አንድ- አንድ ከሆንን ወይም ከተባበርን
ሁለት- በመላ አገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ማስፈን ከቻልን
ሶስት- ምርጫውን ጨርሰን ዝንቅ አስተዳደርና ህይወት ያለው ፓርላማ ከመሰረትን
አራት- አባይን አጠናቅቀን ሃይል ማመንጨት ከጀመርን
አምስት- ከቻይናና ሩስያ ጋር ያለንን ሁለንተናዊ ግንኙነት ካጠናክርን
ስድስት- ያለንን እየተካፈልን ለመብላትና ከምዕራቡ ዓለም የሚገቡ የቅንጦት እቃዎችን ከቀነስን
ሰባት- ባለስልጣኖቻችን እንደ ህዝቡ ለመኖር ከወሰኑ
ስምንት- ዲያስፖራው ስራ እየሰራ አገሩን በታታሪነት ከረዳ
ዘጠነኛ- ህዝቡ በብሄራዊ ስሜት ቁጭት በተለይም ወጣቱ ከምዕራባውያን የስነልቦና ባርነት ተላቆ በራሱ እንዲቆምና ለለውጥ እንዲነሳ ከተቀሰቀሰ እና
አስረኛ- የአፍሪካ ህብረትና ተመድን በመጠቀም ብልጠት የተሞላበት የዲፕሎማሲ ስራ ከተሰራ
ያኔ ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ሳትሄድ አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ትመጣለች። እጃቸውን ስመን ሳይሆን፣ እጃችንን ስመው ይወዳጁናል። ይህ አጋጣሚ ለዘመናት ሰፍኖ የቆየውን የአዛዥና ታዛዥ ግንኙነት ለመስበር ሊጠቅም ይችላል። ፈተናዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም፣ ቆራጥነት፣ ጽናት፣ ብልጠትና አስተውሎ መጓዝን ይጠይቃል።

Read 2262 times