Saturday, 22 May 2021 14:30

የምጡቅ አዕምሮ ባለቤት

Written by  ሻሎም ደሳለኝ
Rate this item
(0 votes)

 የብዙ ሙያዎች ባለቤት: በፈጠራ፣ በሥነ-ሥዕል፣ በንድፍ፣ በአርክቴክቸር፣ በሳይንስ፣ በሙዚቃ፣ በሒሳብ፣ በምህንድስና፣  በሥነ ፅሁፍ፣ በህክምና፣ በክዋክብት ጥናት፣ በዕፅዋት፣ በታሪክ ሌላም ሌላም ሌላም አያሌ ሙያዎች ላይ እውቀት እንዳለው የሚነገርለት። በፓራሹት፣ በሄሊኮፕተር፣ በታንክና የብረትን ቴንሳይል ስትሬንግዝ መለኪያ ማሽኖች ላይ የእሳቤና የንድፍ አሻራው እንዳለ የሚተረክለት። በበርካታ የታሪክ ምሁራን ዘንድ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ባለቤትነቱ የሚወሳለት። እንደውም በታሪክ ድርሳናት ላይ የሱን ያክል ምጥቀትና ጥልቀት  ያለው አቻ የማይገኝለት ሰው ስለመሆኑ የሚነገርለት። ዓለማችን ካሳየችን ሰዎች መሀል በምሳሌነት ከፊት ሊቀመጥ የሚችል ጠቢብ።
ይህ ሰው ሊዮናርዶ ዳቪንቺ ይሰኛል።
ብዙዎች ይሄን ስም ያውቁታል አልያም ሲሰሙት በቶሎ ያስታውሱታል። በተለይ እጅግ ዝነኛ ሥራው  በሚባልለት በቅንድብ አልባነት በምትታወቀው፣ በመሳቅና በመኮሳተር መሀል ሆና በተሳለችው ሥዕሉ ማን እሱን ይዘነጋዋል? ስለ ሞናሊዛ ብዙዎች ገጥመዋል። ሞዝቀዋል። ከትበዋል። ትውልድና እድገቱ ፍሎረንስ በተባለ ስፍራ ነው። ባሁኗ ጣልያን መሆኑ ነው። በምድር ላይ ከ1452 እስከ1519 ድረስ ለ67 ዓመታት ኖሯል። ዕድሜው ሳይሆን ስራው አንቱ አስብለውት አልፏል። በርካታ ታሪክ አጥኚዎች “Universal Genius” or “Renaissance Man”ብለው ይጠሩታል።
“Art Through the Ages” በሚል ታሪክ አዘል መፅሀፏ የምትታወቀው አሜሪካዊቷ ሄለን ጋርድነር ደሞ ሊዮናርዶን በሚያትት ገለፃዋ፤ “እሱ አስደናቂና ልዕለ ሰብአዊ ነው” ትላለች። እውነትም ያስብላል። በአናቶሚ፣ በጂዮሎጂ ፣በሲቪል ምህንድስና በበርካታ ዘርፎች ላይ አሻራው እንዳለ ሲጠቀስ እየሰሙ የአድናቆት ቃል ሲያንስበት ነው ያሰኛል፡፡
ሊዮናርዶ ትምህርቱን ፍሎረንስ ውስጥ ነው የተከታተለው።  አብዛኛውን የስራ ጊዜውን ሚላን ውስጥ አሳልፎታል። በስተመጨረሻ ግን ህይወቱ ያለፈችው ፈረንሳይ ውስጥ በስጦታ ከ Francis I በተበረከተለት ቤት ውስጥ ነበር።
@Monalisa:- The most famous of his work:- The most parodied portrait
@The Last Supper:- The most reproduce religious painting
@Vitruvian Man:- The most cultural icon, reproduce on items like euro coin,textbooks,T-shirtss በመባል ስራዎቹ ጫፍ የነኩ ሲሆን
@Salvator Mundi የተሰኘው ስራው ደሞ በ2017 ኒውዮርክ ከተማ ውስጥ በ $450.3 ሚሊየን መሸጥ ችሏል። ይሄ ሽያጭም በስዕል ጥበብ ታሪክ ትልቅ ዋጋ የወጣበት እንደሆነ ይነገራል።
ከሁሉ በላይ በሰዎች ዘንድ በብዛት የሚታወቀው፣ በብዛት የተጎበኘው፣ ብዙ የተፃፈለት በበርካታ ቋንቋ የተሞዘቀለት (በኛ አገር ጋሽ ጥላሁን ገሰሰን፣ አሊ ቢራን እና ቴዲ አፍሮን ማንሳት ይቻላል) የዓለማችን ድንቅ ስዕል ሞናሊዛ የተሰኘው ስዕል ነው። ይህ ስዕል በ77ሳ.ሜ የቁመት መጠንና በ53ሳ.ሜ የአግድሞሽ ቁመት በተወጠረ ሸራ ላይ የተከተበ ሲሆን ከዓለማችን ውድ ስዕሎች መሃል አንዱ ነው። ለዚህም ይመስላል በ1962 ለዚሁ ስዕል የ100 ሚሊየን ዶላር ኢንሹራንስ የተገባለት። ይህ መጠን በ2018  የኢንሹራንስ ዋጋው ወደ 650 ሚሊየን ዶላር አድጓል። ይሄም በጊነስ ወርልድ ሪከርድ ላይ ቀዳሚ ሆኖ እንዲሰፍር አድርጎታል።
ስዕሉ ተስሏል ተብሎ የሚታሰበው ከ1503-1506 ቢሆንም እስከ 1517 ዓ.ም ድረስ ሊዮናርዶ አሻራውን ሳያኖር አይቀርም ይባላል። አንዳንድ የቅርብ ጊዜ ጥናቶችም፤ ስዕሉ ከ1513 ዓ.ም በፊት እንዳልተሳለ ያትታሉ። ሞናሊዛ የሚለውን ስም የሰጠው ሊዮናርዶ አይደለም ። ይልቁንም የሊዮናርዶን የህይወት ታሪክ  ፅፏል ተብሎ የሚነገርለት Giorgio Vasari እንጂ።
ምንም እንኳን ዛሬ ላይ የስዕሉ ባለቤት ፈረንሳይ ብትሆንም፣ የሰዓሊውን የህይወት ታሪክ እንደዘገበው ሰው ትርክት ከሆነ፤ ሊዮናርዶ ከመሞቱ በፊት ስዕሉን ረዳቱ ለነበረው Salai ለተባለ ሰው አውርሶት ነበር፡፡ በነገራችን ላይ በስዕሉ ላይ ያለችው ሴት Lisa del Gioconda ትባላለች። ፍሎረንስ ውስጥ ይኖር የነበረ Francesco de Giocondo የተባለ ሀብታም የሀር ነጋዴ ሰው ሚስት እንደሆነችና ስዕሉም የተሳለው ጥንዶቹ አዲስ ቤት ሰርተው፣ Andrea የተባለ ሁለተኛ ልጅ ወልደው ስለነበር የደስደስ ገፀ በረከት እንዲሆን እንደነበር  ይነገራል።
ሊዮናርዶ በህይወት ዘመኑ መጨረሻ አካባቢ ፓራላይዝድ ሆኖ ነበርና የሞናሊዛን ስዕል ስሎ አለመጨረሱ ያናድደው ነበር ይባላል። በስተመጨረሻ ግን ፈረንሳይ ውስጥ ስዕሉን መጨረስ ችሏል።

Read 1454 times