Saturday, 22 May 2021 12:21

የአንዱ አለም አራጌ “3000 ሌሊቶች” መፅሐፍ ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የእውቁ ፖለቲከኛና የነፃነት ታጋይ አንዱዓለም አራጌ “3000 ሌሊቶች” መፅሐፍ የፊታችን ሰኞ በግዮን ሆቴል ግሮቭ ጋርደን ዎክ ይመረቃል።
የመፅሐፉ ደራሲ አቶ አንዱ አለም አራጌ እንደገለጹት፤ መፅሐፉ የትናንቱ ልብ ሰባሪ ስህተት እንዳይደገም፣ ወደ ነገው ትውልድም እንዳይሻገር መቃተት ውስጥ የተወለደ ነው።
በመፅሐፉ የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ አምባሳደር ታደለች ኃ/ሚካኤል ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ አቶ ኢቦንግ ሜቶ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ ዑስታዝ አቡበከር አህመድ፣ መጋቢ ሐዲስ  እሸቱ አለማየሁና አቶ አልባኖ ሌሊሳ እንደሚገኙና በመፅሐፉ ዙሪያ ሃሳባቸውን እንደሚገልፁም  የመርሃ ግብሩ አዘጋጆች ተናግረዋል።


Read 3539 times