Saturday, 15 May 2021 00:00

በ”ጊዜ ባርና ሬስቶራንት” ልዩ የሙዚቃ መሰናዶ ዛሬ ምሽት ይቀርባል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 ጊዜ ባርና ሬስቶራንት ዛሬ ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ ልዩ የሙዚቃ ድግስ ማስናዳቱን ገለፀ። በዚህ የሚዚቃ ድግስ ድምፃዊ ታረቀኝ ሙሉ (በባይተዋር ጎጆ)፣ አዲስ ጉልሜሳ (የማህሙድ)፣ አብነት ደምሴ (የማሪቱ) እና ዋሲሁን ረታ (የሙሉቀን) ድምፃዊያኑ ከማህሌት ባንድ ጋር በመጣመር በቀጥታ ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ዳዊት ፍሬው ሀይሉ ሳክስፎን እንደሚጫዎትም የጊዜ ባርና ሬስቶራንት ሃላፊዎች ገልፀዋል።
በዚህ ልዩ ምሽት ከወዳጅ ዘመድ ጋር ቦሌ ማተሚያ ቤት በሚገኘው ጊዜ ጀርባ ባርና ሬስቶራንት መጥተው በመታደም አስደሳች ጊዜ  እንዲያሳልፉ ግብዣ የቀረበ ሲሆን የሙዚቃ ድግሱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ፕሮቶኮል በጠበቀ መልኩ እንደሚካሄድና ቀድመው የመጡ ብቻ እንደሚስተናገዱ ለማወቅ ተችሏል።



Read 945 times