Print this page
Monday, 17 May 2021 10:55

የአመቱ የአለማችን ባለ ከፍተኛ ገቢ ስፖርተኞች ይፋ ተደረጉ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ታዋቂው ፎርብስ መጽሄት ባለፈው የፈረንጆች አመት 2020 እጅግ ከፍተኛ ገቢ ያገኙ 10 ስፖርተኞች ከሰሞኑ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ ታዋቂው ቦክሰኛ ኮኖር ማክግሪጎር በ180 ሚሊዮን ዶላር በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ፎርብስ ባለፈው ረቡዕ ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳስታወቀው፣ የባርሴሎናው አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ በ130 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ሁለተኛ ደረጃን የያዘ ሲሆን፣ የጁቬንቱሱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ120 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ የዳላስ ካውቦይስ ቅርጫት ኳስ ቡድን ተጫዋቹ ዳክ ፕሪስኮት በ107.5 ሚሊዮን ዶላር፣ የሎሳንጀለስ ሌከርሱ ኮከብ ሊቦርን ጄምስ በ96.5 ሚሊዮን ዶላር፣ የፓሪስ ሴንጄርመኑ ተጫዋች ኔይማር በ95 ሚሊዮን ዶላር፣ የጠረጴዛ ቴኒስ ኮከቡ ሮጀር ፌደረር በ90 ሚሊዮን ዶላር፣ የኤፍ ዋኑ ሊዊስ ሃሚልተን በ82 ሚሊዮን ዶላር፣ ቶም ብራዲ በ76 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ኬቪን ዱራንት በ75 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደቅደም ተከተላቸው ከአራተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኞች መሆናቸውንም አመልክቷል፡፡ አስሩ ባለከፍተኛ ገቢ ስፖርተኞች ባለፈው አመት በድምሩ 1.05 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘታቸውን ያስታወቀው ፎርብስ፣ ምንም እንኳን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአለማችን ስፖርት ላይ ክፉኛ ጉዳቱን ቢያደርስም በአስሩ ስፖርተኞች በአመቱ ያገኙት አጠቃላይ ገቢ በአንጻሩ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ28 በመቶ ዕድገት ማሳየቱንም አክሎ ገልጧል፡፡

Read 3438 times
Administrator

Latest from Administrator