Monday, 10 May 2021 00:00

የመከባበርና የመደናነቅ ፕሮግራም ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   በ”ቅን ኢትዮጵያ ማህበር” አዘጋጅነት የተዘጋጀው የመደናነቅና የመከባበር መርሃ ግብር የፊታችን ማክሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።
ማህበሩ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ባዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር አገራዊ የተማሪዎች፣ የመምህራንና የወላጆች የመመሰጋገንና የመደናነቅ መርሃ ግብር የሚካሄድ ሲሆን፣ በዚህ መርሃ ግብር ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የኪነ-ጥበብ ሰዎችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚታደሙ ማህበሩ ገልጿል።
“ቅን ኢትዮጵያ ማህበር” በህዝቦች መካከል ቀና አስተሳሰብ እንዲኖርና በመልካም ስነ-ምግባር የታነጸ ዜጋ ማፍራት ከተቋቋመባቸው አላማዎች ዋነኞቹ ሲሆኑ በጎ አሳቢነት፣ መከባበር፣ መመሰጋገንና መደናነቅ  በሰዎች መካከል በመፍጠር ሰላማዊ ዜጋና የተረጋጋች አገር መፍጠር ይቻላል ብሎ ያምናል ተብሏል።
ከዚህ አኳያ የመደናነቅና የመከባበር ዓመታዊ በዓል ለማዘጋጀትም ጠንክሮ እየሰራ እንደሆነ ማክሰኞ የሚካሄደው መርሃ ግብርም የዚሁ አካል መሆኑንም ማህበሩ አስታውቋል።


Read 9192 times