Saturday, 08 May 2021 12:28

የመራጮች ምዝገባ ለተጨማሪ 7 ቀናት ተራዘመ

Written by  መታሰቢያ ሳሣዬ
Rate this item
(0 votes)

  እስከ አሁን ከ28 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል
            
            በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ፣ የመራጮች ምዝገባ ለሁለተኛ ጊዜ የተራዘመ ሲሆን፡፡ እስከ አሁን ከ28 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል ተብሏል፡፡
ትናንት የተጠናቀቀው የመራጮች ምዝገባ ለተጨማሪ ሰባት ቀናት ነው የተራዘመው፡፡
ቀደም ብሎ ይፋ የተደረገው ቀነ ገደብ የመራጮች ምዝገባ ከአፋርና ከሶማሊያ በስተቀር በትላንትናው ዕለት የሚጠናቀቅ መሆኑን የሚያመለክት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ምርጫ ቦርድ ያለፉት ቀናት ተደራራቢ ብሔራዊና ሃይማኖታዊ የበዓል ቀናት የነበሩበት በመሆኑና መራጩን ህብረተሰብ እንደ ልብ ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችሉ ንኡስ ጣቢያዎችን ለማደራጀት ጊዜ የወሰደ በመሆኑ የምዝገባ ቀኑን ለሁለተኛ ጊዜ ማራዘም እንዳስፈለገ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።
ተቀዛቅዞ የነበረው የመራጮች ምዝገባ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሄዱን ያመለከተው ቦርዱ፤ እስከ አሁን ከ28 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል ብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በ41 ሺ 798 ምርጫ ጣቢያዎች ምዝገባ እስከ መጪው አርብ ግንቦት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ለሰባት ቀናት እንዲራዘም መወሰኑን አስታውቋል፡፡


Read 1044 times