Print this page
Saturday, 01 May 2021 12:18

በአጣዬ እና አካባቢው የተፈፀመው ድርጊት በልዩ መርማሪ አየተጣራ ነው ተባለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

  በቅርቡ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ አጣዬና ሸዋሮቢት እንዲሁም በአካባቢው ባሉ ከተሞች የተፈፀመውን ድርጊት የሚያጣራ ልዩ የምርመራ ቡድን ከፌደራልና ከክልል ጠቅላይ አቃቢና ፖሊስ ተወጣጥቶ ምርመራ መጀመሩን ታውቋል፡፡
የተፈፀመው ድርጊት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ጥልቅ ምርመራ እንደሚካሄድበት ያመለከተው የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ  የምርመራ ውጤቱን ተከትሎም አጥፊዎችን ለህግ የማቅረብ መጠነ ሰፊ ስራ ይከናወናል ብሏል፡፡
ወደ ስፍራው የተሰማራው የምርመራ ቡድን፣ ጉዳዩን በፍጥነት በማጣራት የደረሰበትን ግኝት ለህብረተሰቡ እንደሚያሳውቅም ተገልጿል፡፡
በተመሳሳይ፤ በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ አካባቢ ከቅማንት ማንነት ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር የሚያጣራ ሌላ ቡድን መላኩን የክልሉ አቃቢ ህግ አስታውቋል፡፡
በሰሜን ሸዋ የተላከው የምርመራ ቡድን አጣርቶ የሚያቀርበው ግኝት ፍትህ እንዲሰፍን ከማገዙም ባሻገር የችግሩን ስር መሰረት አውቆ የመጨረሻ መፍትሔ ለመስራት እንደሚያስችልም ታምኖበታል፡፡

Read 11493 times