Saturday, 01 May 2021 12:14

ማንንትን ትኩረት ያደረጉ ግድያዎች አሁንም መቀበላቸው አሳሳቢ ነው ተባለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

   በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን በሚገኙ ለሙኩሳ፣ ቀጮ፣ክርክር እና ጋሌ በተባሉ ቀበሌዎች ውስጥ ሚያዚያ 15 ቀን 2013 በተፈፀሙ ጥቃቶች ቢያንስ ከ20 ያላነሱ ዜጎች ማንነታቸው ተለይቶ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ያስታወቀው ኢሰመኮ፤ የንፁሃን ዜጎች ማንነት ለይቶ ግድያ አሁንም መቀጠሉ በእጅጉ አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡
በተመሳሳይ በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት 6 ሰዎች መገደላቸውን የቆመው ኢሰመኮ፤ የታጣቂዎች ጥቃት መበራከትና መስፋፋት የዜጎችን የመኖር ዋስትና እየተገዳደረ ነው ብሏል፡፡
በየቦታው በታጣቂዎች የሚደርሱት ጥቃቶት መበራከት የፀጥታ መዋቅሩ የመከላከልና የዝግጁነት አቅም ከፍተኛ መሻሻል ሊደረግበት እንደሚገባ ጠቋሚ ነው ብሏል-ኢሠመኮ በመግለጫው።
መንግስት የሰላማዊ ሰዎች ግድያንና ዘር ተኮር ጥቃትን መከላከል የሚያስችሉ ልዩ እቅዶችን ነድፎ እንዲንቀሳቀስ ኢሠመኮ በተደጋጋሚ ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

Read 1794 times