Saturday, 24 April 2021 13:35

“ዋይልድ ኮፊ” ነገ በይፋ ተከፍቶ ስራ ይጀምራል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     የመጀመሪያው ቡና በዶላር የሚሸጥበት ካፌ ነው ተብሏል
                            
          በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኤክስፖርት ቡና መቅመሻ እንደሚሆን የተነገረላትና የራሱን የቡና ጣዕም ቀምሞ ያቀረበው “ዋይልድ ኮፊ” ነገ ረፋድ 3፡00 ላይ በይፋ ተመርቆ ስራ እንደሚጀምር የዋይልድ ኮፊ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ማሞ ገለፁ።
ዋይልድ ኮፊ በተለይ ያራሱን ብሌንድ ቡና በመቀመርና በማደራጀት ባለፉት ሶስት  ዓመታት የተዘጋጀ ቡና ወደ ውጪ ሲልክ እንደቆየ የጠቆሙት አቶ ገዛኸኝ፤ የቡና መቅመሻ ካፌው አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ቱሪስቶችና ሌሎች የውጪ ዜጎች ትክክለኛ ተፈጥሮ ያለውን የኢትዮጵያ ቡና እዚሁ ካፌ ገብተው እንዲያጣጥሙ የምናደርግበት ስፍራ ነው ብለዋል።  ለዚህም በዶላር ከፍለው እንዲጠጡ ከብሄራዊ ባንክ ፈቃድ ያገኘን የመጀመሪያዎቹ ባለ መቅመሻ ቤቶች ነን ሲሉም አብራርተዋል።
ዋይልድ ኮፊ ቦሌ ወደ መስቀል ፍላወር መሄጃ መንገድ ላይ አዲስ በተገነባው ለቤንዝ ታወር ላይ የሚገኝ ሲሆን ቤቱ ከቡና አመጣጥ ታሪኩ ጀምሮ ኢትዮጵያ ለዓለም ቡና በመላክ ዓለምን እያጠጣ ያለችበት ሁኔታ በስዕል የተገለፀበት፣ ቤቱ ውብና ማራኪ ሆኖ የተደራጀበት ሂደት የሚታይ ሲሆን፣ ይህን መቅመሻ ካፌ ለማደራጀትም ከ4.5 ሚ. ብር በላይ መውጣቱን መስራቹ ጨምረው ገልፀዋል።
ዋይልድ ኮፊ በቀጣይ በሳር ቤት “ዲፕሎማቲክ” ቅርንጫፍ፣ ቦሌ ሲቲ ብራንች፣ በፒያሳ አራዳ ኦልድ ሲቲ ብራንች፣ በሲኤምሲ ሲቲ ብራንች የተሰኙ ቅርንጫፎችን የመክፈት ዕቅድ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል። መስቀል ፍላወር መንገድ ላይ የተከፈተውና ዛሬ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሂሩት ካሰው (ዶ/ር) በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው የካፌው ዋናው ቅርንጫፍ ሲሆን በአጠቃላይ ለ22 ሰዎች የስራ  ዕድል መፍጠሩም ታውቋል።
ዋይልድ ኮፊ በሳዑዲ አረቢያ ከ70 በላይ በሆኑ ሱፐር ማርኬቶች የሚሸጥ ሲሆን በኦማን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና፣ ማሊ ጀርመንና፣ አሜሪካ  ቡናው ተቆልቶና ተፈጭቶ በአውሮፕላን የሚላክ በመሆኑ በትኩስነቱ ለፈላጊ አገራት እንደሚያደርስም ተናግረዋል። ዋይልድ ኮፊ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦሪጂን ቡና መቅመሻና የኤክስፖርት ቡና በዶላር እንዲሸጥ የተፈቀደለት በመሆኑ መደሰታቸውን የገለጹት አቶ ገዛኸኝ፤ በቀጣይ የኢትዮጵያ ቡና ጥራቱንና ተፈጥሮውን ጠብቆ በዓለም ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲሆን በርትተው እንደሚሰሩም ተናግረዋል።


Read 1717 times