Print this page
Saturday, 10 April 2021 12:06

የኦንላይን ትምህርት በድግሪ ደረጃ መስጠት ሊጀመር ነው

Written by  መታሠቢያ ካሣዬ
Rate this item
(1 Vote)

   ላይፍ-ማፕ የከፍተኛ ትምሕርት ተቋም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ በመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራም የበይነ መረብ (ኦንላይን) ትምህርት መስጠት ጀመረ። ተቋሙ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ፣ በሁለት የትምህርት ዘርፎች  “በአካውንቲንግ ኤንድ ፋይናንስ” እና “በማኔጅመንት” በበይነ መረብ መስመር የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራም እንዲሰጥ ፍቃድ  ተሰጥቶታል። ፡፡
በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ-መረብ  ስልት (online education system) ትምህርት ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ ምዝገባ መጀመሩን ድርጅቱ በሰጠው መግለጫ ላይ አስታውቋል። የተቋሙ ፕሬዚደንት አቶ ታዬ መሀመድ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ትምህርቱ ብቃት ባላቸው መምህራን በበይነ መረብ የሚሠጥ ሲሆን የተማሪው ምዝገባና ፈተናው ግን በገጽ ለገጽ የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል። ተቋሙ ከከፍተኛ ትምህርትና አግባብነት ኤጀንሲ  ለበይነ መረብ ትምህርት ሙሉ እውቀና የተሠጠው ሲሆን በየጊዜው ቁጥጥርና ክትትል እንደሚደረግበትም ተናግረዋል። ተቋሙ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርት ቤት እየሄዱ መማር ለማይችሉ ሠዎች፣ ጥሩ አማራጭን ይዞ መምጣቱን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፤ በተለይም በተለያዩ የአለማችን አገራት እየኖሩ ትምህርታቸውን ለመማር ያልቻሉ ወገኖቻችን የዕድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።   ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን አጠናቀው በሚመረቁበት ወቅት ከተማሩበት የትምህርት ዘርፍ በተጨማሪ የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ እውቀታቸውም ከፍ ያለ ይሆናል ብለዋል። ትምህርቱ ሁሉም ሰው ከፍሎ መማር በሚችልበት ዋጋ የሚሠጥ መሆኑን ያመለከቱት ፕሬዚደንቱ ክፍያው ለመደበኛ የኮሌጅ ትምህርት ከሚከፈለው ዋጋ ብዙም ያልተለየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ምዝገባው ትላንት ሚያዝያ 1 ቀን 2013 ዓ.ም መጀመሩንም ለማወቅ ተችሏል።

Read 1276 times