Print this page
Saturday, 27 March 2021 12:04

የትግራይ ጦርነት ከ45 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሷል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

            የአሜሪካ የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተል ቡድን ልትልክ ነው
        የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ሁኔታ አሳስቦኛል ያለው የአሜሪካ መንግስት፤ ጉዳዩን የሚከታተል ልዩ ልኡክ ማደራጀቱን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሃላፊው አንቶኒ ብሊንከን ያስታወቁ ሲሆን የትግራይ ጦርነት ከ45 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል፡፡
በቀጣይ ሳምንት በይፋ ስራውን ይጀምራል የተባለው ልኡክ፤ በዋናነት ቀጠናዊ የፖለቲካ  ክረቶች ወደ ቀውስ ሊያመሩ ይችላሉ ተብሎ በተሰጋው የምስራቅ አፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ፣ሱዳን፣ግብጽ መካከል ያሉ አወዛጋቢ ጉዳዮችን በቅርበት ይከታተላል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም በትግራይ ያለውን ግጭት በአንክሮ የሚከታተል ይሆናል፤ ግጭቱ የሚያበቃበትን ሁኔታም ለማመቻቸት ጥረት እንደሚያደርግ  የውጭ ጉዳይ ሃላፊው መረጃ ጠቅሰው  መገናኘ ብዙሃን የዘገቡት፡፡
ትግራይ ያለው ቀውስ በሱዳንና ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው የድንበር ውዝግብ እንዲሁም ግብጽ፣ሱዳንና ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የገቡት እሰጣ ገባዎችም በአሁኑ ወቅት የምስራቅ አፍሪካን ቀጠና ስጋት ውስጥ የጣሉ መሆናቸውን የአሜሪካ መንግስት አመልክቷል፡፡
የአሜሪካ ልኡክ ቡድን የቀጠናውን ሁኔታ በቅርበት ሲከታተል፣ በዋናነት ሰብአዊ ድጋፍ ለዜጎች እንዲደርስ መደገፍ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈፀሙ መከታተል፣ ተፈፅመዋል በሚባሉት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ጥረት ማድረግ እንዲሁም የኤርትራ ሰራዊት ከኢትዮጵያ ለቆ እንዲወጣ ጥረት ግፊት ማድረግ ላይ እንደሚያተኩር የውጭ ጉዳይ ሃላፊው አስገንዝበዋል፡፡
በትግራይ የሚካሄደው ጦርነት ባለፉት አራት ወራት ብቻ የ1 ቢሊዮን ዶላድ (45 ቢሊዮን ብር) ኪሳራ ማድረሱን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሰሞኑን በፓርላማ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

Read 12324 times