Saturday, 27 March 2021 11:42

“ከሱዳን ጋር ጦርነት እንገባለን አንገባም በሚለው ጉዳይ ላይ አሁን መናገር አይቻልም”

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

       የግብጽና ሱዳን ወታደራዊ ስምምነት ኢትዮጵያን አያሰጋትም
                    
          የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ በትዕግስት መያዙን ያስገነዘቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ ከሱዳን ጋር ጦርነት እንገባለን አንገባም የሚለው መናገር አሁን አይቻልም ብለዋል፡፡
ሰሞኑን ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ ኢትዮጵያ የውስጥ ሰላሟን ያጣች የመሰላቸው ሃይሎች ይሔን አጋጣሚ ተጠቅመው የተለያዩ ትንኮሳዎችን መፈፀማቸው የሚደንቅ አለመሆኑን ያወሱት ቃል አቀባዩ፤ በውስጥ የእርስ በእርስ ግጭቶች አትራፊ የሚሆኑ ሃይሎች አሉ ብለዋል፡፡
ግብጽና ሱዳን ወታደራዊ ስምምነትንና ግብጽ ወደ ሱዳን ጦሯን ማስጠጋቷን አስመልክቶም ሁለቱ ሃገራት የጋራ ወታደራዊ ስምምነት መፈራረም ይችላሉ ነገር ግን ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ ኪሰራ ላይ የተመሰረተ ከሆነና የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለመዳፈር ከሆነ በቸልታ አይታይም፤ አሁን ኢትዮጵያ ትዕግስትን የመጀመሪያ አማራጭ አድርጋለች ብለዋል፡፡
አሁን በሃገሪቱ ዳር ድንበር ላይ የሚፈፀመውን ትንኮሳ ተከትሎ ጦርነት ውስጥ እንገባለን አንገባም የሚለውን ጉዳይ ላይ አሁን ላይ መናገር እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡
ሱዳን በዚሁ የድንበር ጥሰትና ወረራ ምን ያህል ኪሎ ሜትር ዘልቃ እንደገባች የጠራ መረጃ እንደሌላቸው ያስታወቁት አምባሳደሩ፤ ነገር ግን በርካታ አርሶ አደሮች ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት መድረሱን ጠቁመዋል።


Read 1096 times