Saturday, 27 March 2021 11:42

ብልፅግና እና ሲአን ለምርጫው ቅንጅት ፈጠሩ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

    ከተመሰረተ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረውና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ  የመድረክ አባል ፓርቲ የነበረው የሲዳማ አርነት ንቀናቄ (ሲአን) እና የብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ፅ/ቤት ቅንጅት መፍጠራቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ከሃምሌ 2012 ጀምሮ እንዴት በክልሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ሲነጋገሩ መቆየታቸውንም የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ ለገሰ ዳንጋም አውስተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ክልሉን እያስተዳደረ የሚገኘው የብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ጽ/ቤት በበኩሉ፤ ሁለቱ ፓርቲዎች ቅንጅት መፍጠራቸው ለክልሉ ተጠናክሮ መቀጠል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብሏል፡፡
 ሁለቱ ፓርቲዎች ቅንጅታቸውን  ያፀኑበት ስምምነትም አንድ በሚያደርጋቸው ጉዳዮች አብሮ በመስራት በሚለያዩባቸው ጉዳዮች ደግሞ ተቻችሎና ልዩነትን አክብሮ ለመስራት መሆኑን የሲአን ፅ/ቤት ሃላፊ  አስገንዝበዋል፡፡
በሃገሪቱም ሆነ በሲዳማ ክልል የተጀመረው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ባለን ፍላጎት መሰረት ነው ከገዢው ፓርቲ ጋር ቅንጅት የፈጠርነው ያሉት የሲአን ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ለገሰ፤ በምርጫው ካሸነፉ ክልሉን በጋራ እንሚያስተዳድሩ አመልክተዋል፡፡

Read 1154 times