Saturday, 13 March 2021 11:57

ኢዜማ “በኦሮሚያ ከምርጫ እንድወጣ ጫና እየተደረገብኝ ነው” አለ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(5 votes)

          “ካድሬዎቹ እጩዎቼን ከማስፈራራት እንዲቆጠቡ መንግስት ትዕዛዝ ይሰጥልኝ”
                    
             የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፤ በኦሮሚያ ክልል ከምርጫው እንዲወጣ የተለያዩ ጫናዎች እየተደረጉበት መሆኑን በመግለፅ በክልሉ መጪውን ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንደማይታዩ ገልጿል።
ብልፅግና ኦሮሚያ ላይ ብቻውን ለመወዳደር አቅዶ እየሰራ ነው ያለው የፓርቲው መግለጫ ይህንኑ የሚያሳዩ በርካታ ነገሮችን እያየን ነው ብሏል።
በመላው አገሪቱ 1385 እጩዎችን አስመዝግቤአለሁ ያለው ኢዜማ፤ በ52 የኦሮሚያ ወረዳዎች ውስጥ እጩዎቼን ለማቅረብ አልቻልኩም ሲል ትናንት በሰጠው መግለጫ ላይ አስታውቋል። ቦርዱ እጩ ማስመዝገብ ባልቻልንባቸው የኦሮሚያ ወረዳዎች ውስጥ እጩዎቻችንን በልዩ ሁኔታ ማስመዝገብ እንድንችል ሊፈቅድልን ይገባልም ብሏል።
ፓርቲው በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የምርጫ ወረዳዎች ውስጥ በእጩነት ያቀረባቸው አባላቱ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነ ጠቁሞ፤ እጩዎቼ ከእጩነት እንዲሰርዙ ወይንም ራሳቸውን እንዲያገሉ በተለያዩ መንገዶች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው ሲል  አቤቱታውን አቅርቧል። ለምርጫው እጩ የሆኑ ሰዎች ያለመከለስ መብት እንዳላቸው እየታወቀ እስርና ድብደባ እያደረሰባቸው ነው ይህንን ሁኔታ መንግስት ሊያስቆምልን ይገባል ሲል በመግለጫው ጠቁሟል።
በምስራቅ ወለጋና በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በቤንሻንጉል ክልል ውስጥ ምርጫን ለማካሄድ የሚያስችል የፀጥታ ሁኔታ መፈጠር አለበት ያለው የኢዜማ መግለጫ፤ መንግስት በየክልሉ ለሚገኙ ካድሬዎቹና ፀጥታ መዋቅሮቹ እጩዎቻችንና አባላቶቻችንን ከማዋከብና ከማስፈራራት እንዲቆጠቡ ጥብቅ ትእዛዝ ሊሰጥልን ይገባል ብሏል።

Read 11851 times