Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 18 August 2012 11:53

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሕልም እውን ሆነ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከጃፓን ቀጥሎ በዓለም የመጀመሪያው የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ድሪም ላይነር፤ የመንግሥትና የአየር መንገዱን ባለሥልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ የቦይንግ ኩባንያ ኃላፊዎችና የክብር እንግዶችን አሳፍሮ ትናንት ጧት የቦሌን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሬት ረግጧል፡፡ ሐሙስ ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስተው ከ12፡30 በረራ በኋላ አዲስ አበባ መድረሳቸውን የጠቀሱት የአውሮፕላኑ አብራሪ ካፒቴን ደስታ ዘርዑ፣ በረራው በጣም ጥሩ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ካፒቴን ደስታ፣ የድሪም ላይነር አውሮፕላን አብዛኛው አካል ከካርቦን ኮምፖሳይት መሠራት ክብደቱን ቀለል ስለሚያደርገው በፍጥነት መጓዝና ብዙ ጭነት መያዝ እንደሚያስችለው፣ ለመንገደኞች ምቾት፣ ለድምፅና ለከባቢ አየር ብክለት ቅነሳ የተሻለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የዘመኑ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ መሳሪያዎች የተገጠሙለት ስለሆነ የአብራሪዎችን ሥራም ማቅለሉንም ካፒቴኑ ገልጸዋል፡፡ አፍሪካ ፈርስት በመባል የተሰየመው ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን ዛሬ ሚኒስትሮችን፣ አምባሳደሮችን፣ የሼባ ማይልስ የወርቅ አባላትና የሚዲያ ሰዎችን ይዞ የመጀመሪያውን የጉብኝት በረራ ወደ ኪሊማንጃሮ ተራራ እንደሚያደርግ አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡ አውሮፕላኑ በክብር እንግድነት የተቀበሉት ም/ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሲሆኑ፣ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደርና የቀድሞው የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ስዩም መስፍን፣ የአሁኑ የቦርድ ሰብሳቢ አዲሱ ለገሠ፣ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚ/ር ድሪባ ኩማ አውሮፕላኑን ይዘው ከመጡ ባለሥልጣናት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

 

 

Read 39943 times Last modified on Saturday, 18 August 2012 12:11