Sunday, 28 February 2021 00:00

ዘንድሮ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት 2 በመቶ ይሆናል፤ አይኤምኤፍ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

  በቀጣይ አመት 8.7 በመቶ እድገት ሊመዘገብ ይችላል
                         
           የዘንድሮ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እድገት 2 በመቶ ይሆናል ሲል የተነበየው አለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF)፣ በቀጣይ አመት በ4 እጥፍ እድገቱ ይጨምራል ብሏል፡፡ በዘንድሮ (2020/21) የኢትዮጵያ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እድገት 2 በመቶ ብቻ እንዲሆን የሚገደደው በኮቪድ-19፣
በአንበጣ መንጋ ጥቃት እና በሃገሪቱ የተለያ አካባቢዎች ባሉ የፀጥታ መደፍረሶች መሆኑን ያመለከተው አ ይኤም ኤፍ፤ እንዲያም ሆ ኖ እድገቱ ከበርካቶች የአፍሪካ አገራት የተሻለ ነው ብሏል፡፡ በቀጣዩ ዓመት ሃገሪቱ ኢኮኖሚ በእጅጉ እድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚገመት የጠቆመው የገንዘብ ተቋሙ፤ ይህን የእድገት ተስፋ ለመደገፍም ብድርና ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክቷል፡፡ ሃገሪቱ ያለባትን ብድር አከፋፈል በተመለከተም የኮቪድ-19 ተፅዕኖና የፀጥታ ችግሮችን ታሳቢ በማድረግ ክለሳና ማሻሻያ መደረጉን ሪፖርቱ ይጠቅሳል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ በምትገባበት ወቅት አሁን ካለው ከአራት እጥፍ በላይ ማለትም ወደ 8.7 በመቶ አመታዊ እድገት እንደምታስመዘግብ አይኤምኤፍ አመልክቷል፡፡ የዓለም አቀፍ የ ገንዘብ ተቋም
ባለሙያዎች በእድገቱ ትንበያ ሪፖርት ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መወያየታቸውን ያመለከተው ሪፖርቱ፤ በተለይ የሸቀጦች ዋጋ መናር፤ የአንበጣ መንጋ ያደረሰው ጉዳት፣  ኮቪድ-19ና የፀጥታ መደፍረስ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት መቀዛቀዝ ዋነኛ ምክንያት መሆናቸው ታውቋል ብሏል፡፡ መንግስት ኢኮኖሚውን በተሻለ እድገት ለማስቀጠል በነደፈው የ10 ዓመት የእድገት እቅድ፤ ሃገር በቀል የኢኮኖሚ ስርአትን በመዘርጋትና የግል ባለ ሃብቱን በመደገፍ
ኢኮኖሚውን ማነቃቃት የሚያስችሉ ስልቶች መንደፉ ተመልክቷል

Read 7910 times