Sunday, 21 February 2021 18:52

“ሰለሞናዊያን” የታሪክ መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

በእውቁ የታሪክ ምሁርና ተመራማሪ ደረሰ አየናቸው (ዶ/ር) የተፃፈውና ከ1262-1521) ድረስ ባለው የመካከለኛው መንግስት ታሪክ ላይ የሚያጠናው “ሰለሞናውያን” የታሪክ መፅሀፍ ለንባብ በቃ።
መፅሀፉ በዋናነት በኢትዮጵያ መካከለኛው ዘመን ታሪካዊ ዳራ፣ በሰለሞናዊን መነሳትና በግዛት ማስፋፋት ዙሪያ፣ በኢትዮጵያ መካከለኛው ዘመን የሲቪል አስተደፋደር፣ በመካከለኛው ዘመን እምነቶችና ፖለቲካዊ ሚናቸውና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው። በ8 ምእራፎች ተደራጅቶ በ376 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ200 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን የመፅሐፉ አዘጋጅ የመጀመሪያ ዲግሪያአቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ትምህርት ሲቀበሉ፣ ሁለተኛ ዲግሪቸውን በፈረንሳይ ሀገር እንዲሁ በታሪክ ሁለተኛ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ሶስተኛ ዲግሪቸውን በአፍሪካ ቀንድ የታሪክ ፍልስፍና ከእውቁ “Paris 1 Pantheon sorbonne” በከፍተኛ ማዕረግ ማግኘታቸውን ታሪካቸው ያስረዳል።
እኚህ ምሁር አጠቃለይ  ጥናታቸው የመካከለናው ዘመን የመንግስት አስተዳደር ላይ ያተኩራል የተባለ ሲሆን፣ በ2002  ከውጭ አገር ዓ.ም ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ዶ/ር ደረሰ፤ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና የድህረ ምረቃ ዲን ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በ2003 ዓ.ም የመካከለኛ ዘመን ታሪክ ድህረ ምረቃ ትምህርት በዩኒቨርሲቲው በመጀመር፣ በአገሪቱ ፈር  ቀዳጅ መሆናቸውንም የግል ታሪካቸው ያስረዳል።

Read 13248 times