Sunday, 14 February 2021 00:00

የፊታችን ሰኞ የምረጡኝ ቅስቀሳ ይጀመራል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(7 votes)

       49 ሺ 407 የምርጫ ጣቢያዎችን አዘጋጅቷል
             
             በግንቦት በሚካሄደው 6ኛው ዙር ብሔራዊ ምርጫ ከትግራይ በስተቀር በመላ ሃገሪቱ 49 ሺህ 407 የምርጫ ጣቢያዎችን  ማደራጀቱን የገለፀው  ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የፊታችን ሰኞ የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
ከፍተኛ ቁጥር ያለው የምርጫ ጣቢያ የተደራጀው በኦሮሚያ ክልል ሲሆን 17 ሺህ 623 ፣በአማራ ክልል 12 ሺህ 199፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል 8 ሺሕ 281፣በሶማሊ ክልል 4ሺህ 57፣በሲዳማ ክልል 2 ሺህ 247፣ በአዲስ አበባ 1ሺህ 848፣በአፋር ክልል 1ሺህ 432፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 699፣በጋምቤላ 431፣ድሬደዋ 305 እንዲሁም በሃረሪ ክልል 285 ናቸው፡፡
በዘንድሮ ምርጫ በአጠቃላይ 50 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በመራጭነት ይመዘገባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የመራጮች ምዝገባም የካቲት 22 ተጀምሮ መጋቢት 21 እንደሚጠናቀቅ ታውቋል፡፡
በምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መጋቢት 22 እና 23 ቀን 2013 የእጩዎች ዝርዝር ይፋ የሚደረግ ሲሆን፣የፖለቲካ ፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ከነገ በስቲያ ሰኞ የካቲት 8 ተጀምሮ እስከ ግንቦት 23 ቀን ይዘልቃል፡፡
ግንቦት 28 በሃገር አቀፍ ደረጃ ምርጫ የሚደረግ ሲሆን በአዲስ አበባና ድሬደዋ ደግሞ ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
የምርጫው የመጨረሻ ውጤት ከግንቦት 29 እስከ ሰኔ 21 ይፋ እንደሚደረግ ታውቋል፡፡

Read 13265 times