Sunday, 14 February 2021 00:00

ኢህአፓ የሱዳንን ወረራ አስመልክቶ ለመንግስትና ለህዝብ ጥሪ አቀረበ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

     ሱዳን በወረራ ከያዘችው የኢትዮጵያ ግዛት ለቃ እንድትወጣ መንግስት ጥንቃቄ የተሞላበት ዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲከተል የጠየቀው ኢህአፓ፤ ድንበሩም በቋሚነት የሚካለልበት መንገድ በአፋጣኝ እንዲመቻች ጥሪ አቅርቧል፡፡
“የገበያ ግርግር ለሌባ ያመቻል” በሚል ርዕሥ የሱዳንን ወረራ አስመልክቶ፣ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ባወጣው የአቋም መግለጫ፤ መንግስት በትግራይ፣ በመተከልና በኦሮሚያ በህግ ማስከበር እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ ሱዳን ድንበር አልፋ ወረራ መፈፀሟ የቆየ የሕወኃት  ተባባሪነቷን ያስመሰክራል ብሏል፡፡
ፓርቲው ለአዲስ አድማስ ባደረሰው በዚሁ መግለጫው፤ ሱዳን አልፋ ወረራ ከመፈጸሟ ጀርባ የህዳሴውን ግድብ የሚያደናቅፍ ተልዕኮ ሊኖር እንደሚችል ጠቁሞ፣ መንግስት ይህን ጉዳይ በጥልቀት እንዲያጤንና አስፈላጊውን ጥንቃቄና እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡
መንግስት በትግራይ የሚያከናውነውን የህግ ማስከበር ሂደት ሙሉ ለሙሉ እንደሚደግፍ የገለፀው ኢህአፓ፤ በወራሪው የሱዳን ሃይል ላይ በሚወሰደው እርምጃ የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነት እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል፡፡

Read 20074 times