Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 11 August 2012 12:35

የሠራዊት ፍቅሬ - “ወርቅ በወርቅ” ፊልም ትዝብቶችና ቅሬታዎች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“ወርቅ በወርቅ” ሲመረቀ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ የሆነውም ይህ ነበር፡፡ ፊልሙን ለመታደም የክብር መጥሪያ ደርሶአቸው ወደ አዳራሹ ለመግባት በር ላይ የተኮለኮሉት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተመልካቾች ሙሉ ሱፍ በለበሱና ቁጥራቸው የትየለሌ በሆኑት የዝግጅት አስተባባሪዎች አቧራ ተነስቶባቸዋል፡፡ካሳንቺስ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አዘውትሮ ለተመላለሰ ሰው ወይ በቶታሉ ቅጥር ክልል በሚገኝ አንድ ጥግ ወይንም ደግሞ ከፊት - ለፊቱ ባለ አንድ ካፌ በረንዳ ላይ አንድ ታላቅ ኢትዮጵያዊን ይመለከታል፡፡ እኚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ በበርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የስኬት ታሪክ ውስጥ ቁጥር አንድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ አንጋፋው አሰልጣኝ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ!

እኚህ ታላቅ የአገር ባለውለታና የኢትዮጵያዊ ውድ ልጅ በጉብዝና ዘመናቸው አንዳችም ነገር እንዳልፈፀሙ ሁሉ የአረጋዊነት ዘመናቸውን በፍጹም ምቾት ሊያሳልፉ ሲገባቸው እንዳለመታደል ሆኖ በዚያችው ካሳንቺስ አካባቢ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ፣ በስተርጅና በየካፌው በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው የሚገፉት ረጅም ሰዓት እንዴት አሰልቺ እንደሚሆንባቸው መገመት ከባድ አይደለም፡፡ ባለፈው ሳምንት በብሔራዊ ቴአትር “ወርቅ በወርቅ” በሚል ርዕስ ለእይታ የቀረበውን የሰራዊት ፍቅሬን ፊልም እንዲመርቁ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ በክብር እንግድነት እንደተጋበዙ ስመለከት በእውነት ልባዊ ኩራት ነበር የተሰማኝ፡፡ ሆኖም ግን …(እመለስበታለሁ)አቧራ ማስነሳት:- በኤፍ ኤም 97.1 ላይ ዘወትር እሁድ በሚቀርበው ርዕዮት በተሰኘ የኪነ - ጥበብና የመዝናኛ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ደራሲና የማስታወቂያ ባለሙያ ሠራዊት ፍቅሬ ባንድ ወቅትበእንግድነት ቀርቦ በጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ፀጋዬ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር፡፡ “ሠራዊት የአንተ መገኘት ባንድ ቦታ ላይ አቧራ ያስነሳል ይባላል፡፡ አጀብና ግርግር ትወዳለህም ይሉሃል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ምን ትላለህ?”በወቅቱ ሠራዊት ለቴዎድሮስ ፀጋዬ ጥያቄ ማስተባበያ የሚመስል መልስ ቢሠጥም እኔም ግን በተለያዩ አጋጣሚዎች ስመለከት ሠራዊት እውነትም ግርግና አቧራ ማስነሳት የሚወድና ደግሞም የሚሆንልት ሰው ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ “ወርቅ በወርቅ” ሲመረቀ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ የሆነውም ይህ ነበር፡፡ ፊልሙን ለመታደም የክብር መጥሪያ ደርሶአቸው ወደ አዳራሹ ለመግባት በር ላይ የተኮለኮሉት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተመልካቾች ሙሉ ሱፍ በለበሱና ቁጥራቸው የትየለሌ በሆኑት የዝግጅትስተባባሪዎች አቧራ ተነስቶባቸዋል፡፡ እነርሱን በመከራ አልፎ ወደ ውስጥ ለመግባት ሲሞከር አንድ አይነት ባንድ ዓይነት የለበሱ በርካታ ቆነጃጅት የፊልም ምረቃውን ወደ ኦስካር ስነ ስርዓትነት የለወጡት በሚያስመስል መልኩ ሌላ ግርግር ይፈጥራሉ፡፡ እነርሱንም አልፎ ወደ አዳራሹ የዘለቀ ሰው ደግሞ የቪ አይ ፒን መቀመጫዎች እናስጠብቃለን በሚሉ ሌሎች አስተባባሪዎች የመገፍተር ዕድል ያጋጥመዋል፡፡ እነርሱንም ሁሉ አልፎ መቀመጫ አግኝቶ የተቀመጠ ሰው ደግሞ እንደተለመደው የፊልም ምረቃ ባህል 1፡00 ያህል ያለምንም ፕሮግራም መቀመጫውን የማሞቅ ግዴታ ይጣልበታል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው እንግዲህ የመድረክ አስተዋዋቂዎች የፊልሙን መጀመር ሊያበስሩ ወደ መድረክ ብቅ ያሉት፡፡ ይህ ነው እንግዲህ አቧራ ማስነሳት ማለት! ከበሮ በሠው እጅ ያምር…ሁለቱ የሬዲዮ ፋና ጋዜጠኞች፡- አንዱአለምና ትዕግስት በሬዲዮ ፕሮግራም የመምራት ልምዳቸውን
ብቻ ተጠቅመው የብሔራዊ ቴአትሩን የፊልም ምረቃት ለመምራት መሞከራቸው ከበሮ በሰው እጅ ያምር ትዝብት ላይ ጥሏቸዋል፡፡ መድረኩን ለመቆጣጠርና ክብር ለሚገባቸው ሰዎች መሰጠት ያለበትን ክብር ተመልካቹ እንዲሰጥ ለማስቻል የአጋፋሪነት ስራው ከብዶአቸው አምሽቶአል፡፡
ባጠቃላይ የሁለቱም የመድረክ አመራር ብቃት የደከመና የተመልካችን ቀልብ መሳብ ነበር፡፡ የክብር እንግዳው (ተመለስኩበት)የመድረክ አስተዋዋቂዎቹ የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ መሆናቸውን ገለፁልን፡እንዲያውም ደራሲው ሠራዊት ፍቅሬን ወደ መድረክ በመጥራት፣ ፊልሙን ለመመረቅ ዶ/ር ወልደመስቀል ለምን እንደተመረጡ እንዲያብራራ ዕድል ሰጡት፡፡ ሠራዊትም በፍሬም ውስጥ የተደረገና የ”ወርቅ በወርቅ”ን ፖስተር የያዘ፣ ዶ/ሩ የአገር ባለውለታ መሆናቸውን የሚያስታውስ፤ እንደዚሁም ፊልሙም ለእርሳቸው ክብር መታሰቢያነት እንደሆነ የሚገልጽ ጽሑፍ የሰፈረበት ስጦታ አበረከተላቸው፡፡ ሕዝቡም አጨበጨበ፡፡ ሆኖም ግን ፊልሙ ሲጀምር እንደታዘብነው በመግቢያው ላይ ይህ ለዶ/ሩ መታሰቢያነት ነው የተባለው ነገር ባለመጠቀሱ ፊልሙ በሌላ ቀን ሲታይ ለዶ/ሩ መታሰቢያ መሆኑን ለማወቅ አይቻልም፡፡ ስለዚህ ዶ/ሩም የአቧራው ፀበል ደርሶአቸዋል ማለት ነው፡፡ የፊልሙ አጀማመር:- ፊልሙ እንደተጀመረ የምስልና የድምፅ ጥራት ችግር አጋጥሞታል፡፡ የድምጽ ጥራቱ ፈጽሞ ያልተዋጣለትና እስከመጨረሻው ድረስ አብሮ የዘለቀ ችግር ሆኖ ታይቷል፡ ምስሉ እያደር ቢጠራም ካሜራው ግን አልፎ - አልፎ ከፍሬም የመውጣት ችግር ነበረበት፡፡ ከድምፁ የጥራት ጉድለት የተነሳ አንዳንዶች እንዲያውም ግማሽ ፊልም አየን ሲሉም አማረዋል፡፡
የፊልሙ ታሪክ:-
ታሪኩን በዝርዝር በመተረክ የፊልሙን ይዘት መናገሩ የታሪኩን አጓጊነት ስለሚጐዳው ጠቅለል እያደረግሁ ሃሳቤን ለማቅረብ መርጬአለሁ፡፡የለንደንን ኦሎምፒክ ታክኮ የተሠራው ፊልሙ፤ ስለ አንዲት ታዋቂ ኢትዮጵያዊት አትሌት የሚተርክ ሲሆን አትሌቷ ውድድሯንበድልእንዳታጠናቅቅ
ስለሚደረግባት ሴራ የሚያሳይ ነው፡፡
አሰልቺነትና ተደጋጋሚነት:-
በተለያዩ ጊዜያት ለእይታ የበቁት ሶስቱም የሠራዊት ፍቅሬ ድርሰቶች የጭብጥ ተመሳሳይነት አለባቸው፡፡ “ሠማያዊ ፈረስ”፣ “ሄሮሽማ”ና “ወርቅ በወርቅ” ሁሉም አንድን ገፀ ባህሪ የአገር ተቆርቋሪ ያደረጉና የእርሱ/የእርሷ ዓላማ ከግብ እንዳይደርስ ለማሰናከል ሌት ተቀን የሚተጉ ሀብታሞችን
የማሳየት አሠልቺነት ይታይባቸዋል፡፡ በ”ሠማያዊ ፈረስ” የእነ ኪሮስና የእነ ታምሩ ብርሃኑ ቡድን (የትወና ስማቸውን ስላላስታወስኩ ነው)”ሄሮሽማ” የእነ አበበ ባልቻ ቡድን፣ በዚህ በ”ወርቅ ለወርቅ” ፊልም ደግሞ የእነ ሽመልስ በቀለ ቡድን፡፡ ይህንን አሠልቺነት ተመልካች ሶስቱንም ፊልም ከተመለከተ በሚገባ ሊያስተውለው ይችላል፡፡ ይህም ደራሲው ሰራዊት ፍቅሬ በዚህ ዓይነቱ ጭብጥ ብቻ በፍቅር የወደቀ መሆኑን በሚገባ ያሳያል፡፡
የፊልም ሞኖፖሊ:- ሠራዊት ፍቅሬና ቴዎድሮስ ተሾመ በአገሪቱ ሌሎች ባለሙያዎች ፈፅሞ የሌሉ ይመስል የፊልሙን ኢንዱስትሪ ለብቻቸው ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ጥረት አንዳንዴ አሣፋሪ ነው፡፡ እንደተለመደው ሁሉ የዚህም ፊልም ደራሲና ፕሮዲውሰር ሠራዊት ሲሆን ዳይሬክተሯ ደግሞ ባለቤቱ ሮማን ናት፡፡ ይህም ፊልሙ የተለየ አተያይ እንዳያመጣ ጋሬጣ ሆኖበታል፡፡ ባልና ሚስት በአንድ ላይ አይስሩ የሚል አቋም የለኝም፡፡ ሆኖም ግን የብዙ ባለሙያዎችን ግብዓት የሚፈልገውን ፊልም በሞኖፖሊ መያዙ ውጤቱ እንደነ “ወርቅ በወርቅ” የብዙ ጉድለቶች ጥርቅም መሆን ብቻ ነው፡፡ ሞኖፖሊው ጭራሹንም ጐልቶ ይወጣና በፊልሙ መሃል በሚቀርቡ ማስታወቂያዎች ውስጥ (የፊልሙ አንድ አካል ተደርገው የቀረቡ ናቸው) በፊልሙ ላይ አሰልጣኝ ሆኖ ሲተውን የምንመለከተው ሠራዊት በማስታወቂያዎች መሃልም ልጅ አቅፎ ወጣት መስሎ ሲሰራ እናየዋለን፡፡
ቢያንስ ያንን ክፍል ቆርጦ ማውጣት ወይንም በሌላ ሰው መተካት ችግሩ ምን ይሆን?ባንዲራዋን ረግጣ የሮጠች አትሌት:- ዋና የፊልሙ ገፀ ባህሪ ሆና የተሳለችው አትሌት የትወና ብቃትዋ እንዳለ ሆኖ በፊልሙ ላይ የተሰጣት ሚና ግን አወዛጋቢ ነው፡፡ ፊልሙ በአገራችን የአትሌቲክስ ታሪክ ላይ ተንተርሶ የተሰራ ነው ከተባለ ገፀ ባህሪዋ ልክ እንደአጐትዋ ሁሉ የኦሮሞ ቅላፄ ያላት፤ ባህልና ክብሯን የምትጠብቅ፣ አብዛኛውን ውጤታማ አትሌቶችን የምትወክል ሆኖ ለምን እንዳልተቀረፀች ደራሲውን መጠየቅ እፈልጋለሁ፡፡ ኦሎምፒክን የመሰለ ከባድ ውድድር ከፊቷ ተደቅኖባት ወደ አንድ ጐረምሳ ቤት ልምምድ እያቋረጠች በተደጋጋሚ ጐራ በማለት ሪከርድ ልትሰብርበት የምትችልበትን የልምምድ ጊዜ ስትቀልድበት ተመልክተናል፡፡ ደራሲው ቢገነዘብ ለሩጫ ተወዳዳሪዎች ደቂቃዎች አይደለም ሰከንድ ያላትን ዋጋ የኃይሌና የፖልቴርጋትን አንድ ወቅት የአንገት ላንገት ትንቅንቅ በማየት ብቻ ማስተዋል ይችል ነበር፡፡ ፊልሙ ይህቺው አትሌት ወደ ኦሎምፒክ ለሚሄዱ ለእራሷና ለጓደኞቿ ክብር በተዘጋጀው የአሸኛኘት ፕሮግራም ላይ አባት አርበኛው ያስረከቧትን ባንዲራ ረግጣ፣ በቅጡ እንኳን ያላወቀችውን ወንድ በማስበለጥ ከአዳራሽ ስትወጣ የሚያሳይ አሳፋሪ ትእይንት ይዟል፡፡ የአገርና የባንዲራን ጭብጥ ይዞ የተነሣ ፊልም፣ ባለማወቅ ባንዲራና አገርን ሲያጣጥል ማሳየቱ የሚያሳፍርና የሚያሸማቅቅ ነው፡፡ አትሌቷ ጋዜጠኞችንም ረግጣ ወደ ጐረምሣዋ ብቻ ሮጠች፡፡ ጐረምሣዋን አግኝታ የተረጋጋች ጊዜ ልክ ቀጥራ እንደምታስተዳድራቸው ሁሉ ጋዜጠኞቹን በእጅ ምልክት በመጥራት ከሠበሰበቻቸው በኋላ እንደገና መግለጫ ለመስጠት ተዘጋጀች፡፡ ይህም ቢያንስ የጋዜጠኝነትን ሞያና ስነምግባር ካለማስተዋል የመነጨ ድፍረት ነው፡፡ ከጋዜጠኝነት ጋር በተያያዘ በፊልሙ ላይ ጋዜጠኛ ሆኖ የሚተውነውን ታደለ አሰፋን፣ ሽመልስ በቀለ የሚጫወተው ገፀ - ባህሪ “አህያ” ብሎ ፀያፍ ስድብ ሲሰድበው ፊልሙን በአዳራሹ ተቀምጦ ሲከታተል የነበረው ጋዜጠኛ ታደለ አሰፋ ምን ተሰምቶት ይሆን?የቫይታሚን ክኒን ለአትሌቷ እንድታስውጥ ሊያውም የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ጨምሮ እያወቋት፣ ከባድ ሐላፊነት የተሰጣት ልጅ በገንዘብ በመደለል እግርን የሚያብረከርክ ሌላ ክኒን እንድትሰጣት ማግባባትና ማስገደድ የሴራውን ልልነት ይጠቁማል፡፡ ለመሆኑ ክኒን ሰጪዋ አትሌት አንዲት ነገር ቢደርስባት ዋነኛና ብቸኛ ተጠያቂ እንደምትሆን ማገናዘብ ያቅታታል እንዴ? ታዲያ በአገር ክህደት ሊያስጠይቃት የሚያስችል ወንጀል ሰርታ የት ሆና ገንዘቡን ልትበላው ነው? አትሌቲክስፌዴሬሽን “ሰላጣ” ለአትሌቶች ባጀት መድቦ እንደሚያዘጋጅም የሰማነው በዚሁ አስገራሚ ፊልም ላይ ነው፡፡ የአትሌቱና ከአሜሪካ ጩኸትና ግርግር ሰልችቶት አገሩ መጥቶ ከብት ማደለብ የጀመረው የመላከ ፍቅር እንዲህ በዝባዝንኬ ባይሸፈን ኖሮ ራሱን የቻለ ምርጥ ፊልም ይወጣው እንደነበር ከአንዳንድ
የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ከአዳራሹ ስወጣ ተወያይቼበታለሁ፡፡ ሰራዊት ቢሆንለት:- እስከዛሬ አራት ሺህ ማስታወቂያዎችን እንደሰራ የተነገረለት ሰራዊት ፍቅሬ፤ አሁን ባፈራው የገንዘብ አቅምና ረጅም የስራ ልምድ ጥሩ ጥሩ የፊልም ስክሪፕቶችን በመግዛት ወደ ዳይሬክተርነቱ ቢያተኩር
ይበልጥ ያዋጣዋል ባይ ነኝ፡፡
====================================
የአገርና የባንዲራን ጭብጥ ይዞ የተነሣ ፊልም፣ ባለማወቅ ባንዲራና አገርን ሲያጣጥል ማሳየቱ የሚያሳፍርና የሚያሸማቅቅ ነው፡፡ አትሌቷ ጋዜጠኞችንም ረግጣ ወደ ጐረምሣዋ ብቻ ሮጠች፡፡

 

 

Read 5118 times Last modified on Saturday, 11 August 2012 12:47