Saturday, 30 January 2021 16:05

አይቤክስ ኮሌጅ ዛሬ ተማሪዎቹን ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ከተቋቋመበት ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ በሆቴል ማኔጅመንትና በሌሎች የቴክኒክና ሙያ ዘርፎች ተማሪዎችን አስተምሮ በማስመረቅ በየዘርፉ የተማረ የሰው ሀይል እጥረትን ሲቀርፍ የኖረው አይቤክስ ኮሌጅ ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ቦሌ አትላስ አለፍ ብሎ በሚገኘው ማግኖሊያ ሆቴል ተማሪዎቹን ያስመርቃል።
በዕለቱ በሆቴል ማኔጅመንት በዲግሪ ፕሮግራም፣ በቴክኒክና ሙያ ዘርፎች ደግሞ በአካውንቲንግ፣ በማርኬቲንግ፣ በእንግዳ አቀባበል እንዲሁም በምግብና መጠጥ መስንግዶ ከደረጃ 1-4 እና “CETNT” ከተሰኘው የሶፍትዌር አምራች ኩባንያ ጋር በመተባበር በብቸኝነት በ “CENT” 1 ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች እንደሚያስመርቅ የኮሌጁ ዲን አቶ ተስፋዬ አሰፋ ለዲስ አድማስ ገልፀዋል። በዕለቱ በቱሪዝም ኢትዮጵያ የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ባንጃው በክብር እንግድነት የሚገኙ ሲሆን፣ ተመራቂ ተማሪዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶች የሚታደሙ ሲሆን የምረቃ ስነ-ስርዓቱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርትና የጤና ሚኒስቴር ያወጡትን የምረቃ ስነ-ስርዓት ፕሮቶኮል ጠብቆ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በመጠንቀቅ እንደሚካሄድ ኮሌጁ ዲን ጨምረው ገልፀዋል።
አይቤክስ ኮሌጅ ባለፉት 12 ዓመታት በርካታ የሰለጠነ የሰው ሃይል ከላይ በተገለጹት ዘርፎች አሰልጥኖ በማስመረቅ በተለይም በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ያለውን የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት ከመቅረፍ አኳያ ጉልህ ሚና እንደነበረው አቶ ተስፋዬ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Read 11380 times