Saturday, 16 January 2021 11:28

“የሀገሬ ጥያቄ 2” የኪነ ጥበብ ምሽት ዛሬ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት በየወሩ የሚካሄደው የኪነ ጥበብ ምሽት የዚህ ወር መሰናዶ “የሀገሬ” ጥያቄ 2” በሚል ርዕስ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንደሚካሄድ የሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ዓለሙ ገለፀ፡፡
በዕለቱ ግጥም፣ ወግ፣ ዲስኩርና ሙዚቃ ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን፣ ሙሃዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ የፍልስፍና ምሁሩ ዮናስ ዘውዴ፣ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም፣ ጋዜጠኛና ገጣሚ ደመቀ ከበደ፣ ገጣሚያኑ አደም ሁሴን፤ ኢሳያስ ባንጫ፣ ኤሊያስ ሽታሁንና አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ የመግቢያ ዋጋው 100 ሲሆን የቪአይፒ 200 ብር መሆኑንና ትኬቶቹ በጃፋር፣ በዮናስ፣ በዘውዱ መፅሀፍትና ስቴዲየም በሚገኘው የእውቀት በርና በካዛንቺስ ጦቢያ መፅሀፍት መደብሮች እንደሚገኙም ታውቋል፡፡

Read 3145 times