Saturday, 09 January 2021 11:34

የወለጋ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ኢሰመጉ አመለከተ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

 በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያየ አካባቢዎች እየደረሰ ያሉ ግድያዎች፣ ድብደባና ማሰቃየት እንዲሁም ህገ ወጥ እስራት ከጊዜ ወደ ጊዜ በአስጊ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አመለከተ፡፡
በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ኢሰመጉ በየሳምንቱ በሚያከናወነው የዳሰሳ ጥናት መረዳቱን አስታውቋል፡፡
በዋናነት በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ኢትዮጵያ በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት አጠባበቅ ተስማምታ ፈርማ ከተቀበለቻቸው መካከል የሰዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ በማናቸውም ቦታ በህይወት የመኖር መብት እየተጣሰ መሆኑን ነው ኢሰመጉ የጠቆመው።
በምዕራብ ኦሮሚያ ምስራቅ ወለጋ፣ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ወለጋ ዞኖች ስር ባሉ አካባቢዎች የክልሉን መደበኛ ፖሊስና ልዩ ሃይሎች ጨምሮ ታጣቂ ቡድኖች በሚወስዷቸው ንፁሃንን ያለየ እርምጃ የበርካቶች ህይወት እየተቀጠፈ ነው ብሏል ተቋሙ።
በክልሉ መደበኛ ፖሊስና ልዩ ሃይል እንዲሁም ታጣቂ ቡድኖች በሚወሰዱ እርምጃዎች፣ በርካቶች ከፍርድ ውጪ መገደላቸውን ለእንግልትና ህገ ወጥ እስራት መዳረጋቸውን ኢሰመጉ ሪፖርት አድርጓል፡፡
በዚህ ግብታዊ የሰብአዊ መብትን ያላከበረ እርምጃ፣ የመኖሪያ ቤቶችና የዜጎች ንብረት እንዲቃጠሉ መደረጉን፣ ችግሩም ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መሆኑንና አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ኢሰመጉ አሳስቧል፡፡

Read 12128 times