Wednesday, 30 December 2020 09:23

«ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ በምድርም ይሁን»

Written by  ሌሊሳግርማ
Rate this item
(0 votes)

 "--ህግ እንደ እግዜሩ ለማስተዳደር፣ ማህበረሰቡ ራሱ ህግ አክባሪና አስከባሪ ሆኖ እንዲሰለጥን ያስፈልጋል፡፡ እንደዛ ሆኖ የሰለጠነ ዕለት ግን ህግ አስከባሪው መንግስት ሳይሆን ህዝብ ራሱ በትክክለኛው ይሆናል፡፡ የህግ አምላክን የሚፈራ ትውልድ ይፈጠራል፡፡--"
             
            የእግዚአብሄርመንግስትአለወይስየለም?ብለህእስክትፈላሰፍድረስሚስጥራዊነው፡፡
«Thatgovernmentisbestthatgovernsleast»የሚለውመፈክር፣በእግዚአብሔርመንግስትላይነውየሚሰራው፡፡ከሰማይበነጎድጓድእየወረደበሆነባልሆነውአያሸብርህም፡፡ዘመቻአያበዛም፡፡ፕሮፓጋንዳአይነዛም፡፡እዩልኝስሙልኝብሎበአደባባይአይቆምም፡፡ግንስራውንይሰራል፡፡
«ምንምወይምጥቂትብቻየሚያስተዳድርመንግስትነውምርጡመንግስት»የተባለው፣ስራውንሳይታይስለሚሰራነው፡፡ዜጎቹን፣ሳይታይናሳይዳሰስ፣ ሳያቅራራናሳያስፈራራእየጠበቃቸውእንደሆነእስኪዘነጉድረስሚስጢርየሆነማለትነው፡፡
መላዕክት፣ለእያንዳንዱሰውጠባቂነትበነፍስወከፍተደልድለውተልዕኮአቸውንያከናውናሉ፡፡ግንስለማይታዩናስለማይዳሰሱጥበቃእየተከናወነእንደሆነይረሳል፡፡ ተጠባቂውነፃነትይሰማዋል፡፡ይሄንንነፃነቱን፣በራሱፈቃድናምርጫለመልካምግብወይምለእኩይያውለዋል፡፡የነፃነቱባሪያሆኖወደአሉታዊነፃነትእንዳይወድቅከራሱተሞክሮይማራል፡፡
የግለሰቡህልውናእንዳይጎዳነፃነቱእንዳይነካአድርጎበስውርይጠብቀዋል፡፡እንዲሁምጥሩመንግስትማለትበዜጋውህይወትላይጣልቃየማይገባማለትነው፡፡በዜጋውህይወትላይጣልቃመግባትየሚችለውህግብቻነው፡፡መንግስትማለትህግየሚያስከብርማለትነው፡፡ህግንየሚያከብርዜጋእስካልበዛድረስመንግስትስውርነው፡፡መንግስትየህግንስጋለብሶ፣መከላከያወይምፖሊስ፣ አልያምደህንነትሆኖየሚከሰተውህግስትጣስብቻነው፡፡ህግካልተጣሰመንግስትመታየትየለበትም፡፡የማይታይመንግስትግንስራውንአይሰራምማለትአይደለም፡፡ዜጋውንሳይታይሳይዳሰስከሚመጣበትመጻኢአደጋይታደገዋል፡፡ዜጋውየሚተዳደርበትህግየሚታይመንፈስእንዳይሆን፣ በየጊዜውጤንነቱንእየጠበቀብርቱሆኖመኖሩንያረጋግጣል፡፡መንግስትየማይታይመንፈስሆኖ፣ህግናየመንግስትስርዐትግንህያውሆነውበማህበረሰቡየዕለትተዕለትህይወትላይእንደእስትንፋስወይምእንደደምመዘዋወርአለባቸው፡፡
ማህበረሰብእንደልብስገበርየውስጡወደውጭመገልበጡየሚታወቀው፣ድብቅመሆንየሌለበትየውስጥአሰራርበይፋሽፋንላይወጥቶሲያስፈራራነው፡፡ ሚስጢራዊነቱሲጠፋ፡፡ደግሞምያስፈራራል፡፡ያውምበትልቅአቅም፡፡አስቡትእስቲ፣የአንድሰውአካልየውስጥአሰራርስርዐትለምሳሌሳንባ፣ ልብናሆድእቃውበስተውጭበኩልበተገላቢጦሽቢወጣ፣ ቆዳውናየውስጥሽፋኑደግሞወደውስጥቢደበቅ፣ ቢገለበጥ፡፡
አምባገነንነትማለትየማህበረሰብየአሰራርስርአት፣የውስጡወደውስጥመገልበጥማለትነው፤መዛባት፡፡ጀርመንበኮሙኒስትናበካፒታሊስትጎራተሰንጥቃበኖረችበትዘመን፣ከበርሊንግንበስተምስራቅእንደዛውስጡወደውጭየተገለበጠአምባገነንነትነበረ፡፡ ህዝብበፍርሃትተደብቆወደውስጥገብቶየመንግስትአሰራርአካላት … ካድሬዎቹ፣ ድብቅፖለሶቹ፣ ሚሊተሪው…ወዘተነበርውጪውንተቆጣጥሮትየኖረው፡፡
የህዝብንደህንነትለመጠበቅቆመናልየሚሉየሚስጢርፖሊሶችዋናስራቸው፣ህዝቡንማሸማቀቅናመሰለልነበር፡፡ የፈለጉትንሰውጠርጥረውለማሰርምክኒያትአያሻቸውም፡፡የሚጠቀሙትህግራሱለዚሁግባቸውእንዲያመቻቸውአድርገውያዘጋጁትነው፡፡እነዚህየስለላፖለሶች «ስታርዚ» ተብለውይጠሩነበር፡፡የማንንምዜጋየመኖሪያበርበአስፈለጋቸውሰዐትአስከፍተውይፈትሻሉ፡፡ የቤቱባለቤትበሌለበትየሚያደርጉትፍተሻይበዛል፡፡ የቤቱባለቤትከሄደበትተመልሶሲመጣ፣እቃውተተራምሶካገኘሌባእንዳልሆነያውቃል፡፡መንግስታዊሌባቤቱእንደገባሲያውቅ«ምንአጥፍቼይሆን?» በሚልጭንቀትተውጦይቀመጣል፡፡ማብራትናማጥፋትበደንብበተደነገገመስመርየተለያዩነገሮችአይደሉም፡፡የአጥፊነትመስመርየቱጋእንደተሰመረዜጋውአይውቅም፡፡ምንቢያደርግእንደሚታሰርበግምትደረጃቢያውቅእንኳን፣ መስመሩግንአስተማማኝስላልሆነድንበሩንአስፍቶ፣ማንንምጥፋተኛአድርጎሊከስይችላል፡፡
የእግዜሩመንግስትሳይታይማስተዳደሩነውግሩምነቱብያለሁኝ፡፡የሰይጣንመንግስትደግሞየሚያስተዳድረውከሚገባውበላይገዝፎበመታየትነው፡፡ የሰይጣንመንግስትአምባገነንነው፡፡«ነፃያወጣሁህእኔነኝ»ብሎሲነግርህ፣ከመስማማትውጭምንምአማራጭየመውሰድእድልአይሰጥህምም፡፡የምትናገረውን፣የምታስበውን፣የምትሰራውንናየምትኖርበትንሁሉየሚወስንልህእሱብቻነው፡፡ የሚወስንልህንሽረህወይምችላብለህእንዳትገኝለማድረግ፣ሁሌህልውናውንከሆነውበላይአግዝፎበመሃልህይገኛል፡፡ይንጎማለላል፡፡መኖሩንፈፅሞእንዳትዘነጋአብዝቶ"አለሁአለሁ"ይልሃል፡፡ወታደርናመዐረግየደረደረባለስልጣን፣ከነደንብልብሱ፣በማህበረሰቡአደባባይይበዛል፡፡ጉበት፣ልብናሳንባወደውጭ…ዐይን፣ጆሮ፣ አፍናአፍንጫበተገላቢጦሽወደውስጥ!ማየትየሚችለውእንዳያይወደሆድእቃ፣ማየትየማይችለውደግሞበተገላቢጦሽየውስጥአካልአምባገነንሆኖወደወጪይወጣል፡፡ማየትስለማይችል፣ በራሱዜጋናአካልላይእያከናወነያለውጭቆናቀስበቀስእንደሚገድለውአይገባውም፡፡ኢ-ተፈጥሮአዊበመሆኑጊዜውንጠብቆህዝብይነሳበታል፡፡ ሆድእቃውስጥገብቶእንዲደበቅየተደረገውህዝብወደውጭይወጣል፤አፈናውሲበዛ፡፡የምስራቅጀርመንህዝብምከእለታትአንድቀንተነስቶወደበርሊንግሄደ፡፡ ባለውመሳሪያተረባርቦ፣ያንንየአፈናተምሳሌትየሆነግንብአፍርሶ፣ወደድሮውቦታተመለሰ፡፡
የእኛምሀገርተመሳሳይነው፡፡… ምንምሳያድግአድገሃልእየተባለሲዘበትበትናሲጨፈርበትየነበረህዝብ፣ ሆድእቃውስጥሆኖየግድእንዲያደምጥይገደድነበር፡፡ … የሰላዩ፣ የወሬአቀባዩ፣የጠርናፊው፣የስነልቦናልምጩ፣ የ"ሂድአትበለው፣ እንዲሄድአድርገው" እስትራቴጂው፣ የገድሎተስፋመስጠትአሻጥሩ… ውጪውላይገኖነበር፣ ህግናዜጋውግንበተገላቢጦሽወደሆድእቃውእንዲገቡሆነ፡፡ሆድውስጥገብተውእርስበእርስመበላላቱ፣በቂምሬትላይሲደርስሚዛንተገለበጠ፡፡ ህዝብወደአደባባይአምባገነን፣ወደመጥፊያውሸሸ፡፡«የታላቁንመሪ»ፎቶበአደባባይሰቅሎህዝብንበማሳቀቅመግዛትለጊዜውቀላልነው፡፡ መሳሪያየያዙናበጦርሜዳላይብቻማገልገልያለበትትጥቅያነገቡ፣ሰራዊትንበከተማመሃልበማንሸራሸርህዝብንበብረትቦክስመግዛትቀላልነው፡፡ ቀላልሆኖምበስተመጨረሻግንአያዛልቅም፡፡በመሰረቱማሰይጣንምማንነቱንያገኘውእኮህግንለመጀመሪያጊዜበመተላለፉነው፡፡ወይምትክክለኛውንህግለራሱየስልጣንጥምሲልበመገልበጡ፡፡ህግ፡-የዜጎችንህይወትመጠበቂያናማበልፀጊያበመሆንፋንታ፣ በስልጣንላይያለውንተቀማጭየግልፍላጎትናጥቅምማስከበሪያወደመሆንሲዞር፣ ያኔ «…The law is pereverted!, The law became the tool of every kind of avarice instead of being its check»ይላሉእነፍሬድሪክቤስቲያት፡፡ህግየስልጣንፍላጎትመግሪያ፣የግለሰብናየማህበረሰብመብትግንማስከበሪያነው፡፡የሰውልጆችንማህበረሰብየሚያደርገውህግነው፡፡ህግግንስልጣንናቅሚያንለማስጠበቂያሲውል፣ያኔ፣ ማህበረሰብንአንድየሚያደርገውተቃውሞናእንቢባይነትይሆናል፡፡ደህንነትየተባለየመንግስትየህግክንፍ፣ህዝብደህንነትእንዳይሰማው፣እርስበራሱእንዳይተማመን፣ በረባባልረባውእንዲናከስለማድረግ፣ከህዝብበተሰበሰበቀረጥሌትተቀንየሚተጋከሆነ፣ህግእውነትምፈፅሞተዛብቷል፡፡ ውስጥሆኖጥቅልአካሉንለማገልገልየተፈጠረውሳንባ፣ ጉበትናልብ፣ወደውጪተገልብጦወጥቷልማለትነው፡፡
አሁንእየታዩመስለውኝየነበሩየለውጥጭላንጭሎችሙሉለሙሉመክነዋል፡፡ሰይጣንገናአልተባረረም፡፡ አባራሪውንናተባራሪውንበግብርመለየትየማይቻልበትደረጃላይደርሰናል፡፡ ሰይጣንሲሰራበትየነበረውየመሰሪነትስርዐትበባህልደረጃእስኪጎለብትተጣብቶስለቆየ፣ በቀላሉወደቦታውአይመለስም፡፡ ዘላቂጤናለመላውሀገርወይምአካልአያሰፍንምእንጂጠማማህግምስርሰዶይቆያል፡፡
አዎ፤ህግንበመፅሐፉመሰረትማስከበርከባድነው፡፡ህዝብንተደበቅሳትል፣በወታደርናበብረትሽታየአየሩንጠረንሳትመርዝጥበቃንማከናወንከባድነው፡፡ ስራውየሚቀለውማአምባገነንሲኮንነው፡፡ጎዳናላይያለውንወጣትአፍሶባለስልጣንንማንምበሌለበትጎዳናማሳለፍጥበቃውንያቀለዋል፡፡ ህግንአዛብቶየህግማስከበርስራንማቅለልይቻላል፡፡ትንንሽሰዎችንገርፎ፣አስሮ፣ወይምበስነልቦናአሸማቆየሚያስፈራህንየባላንጣአደጋመቀነስይቻላል፡፡ ግንአደጋውበዝቶናተጠራቅሞይመጣና፣ አንተባፈረስከውህግመዳኘትየማትችልበትአጣብቂኝውስጥይጥልሃል፡፡
በትክክለኛውህግእንደእግዜሩለማስተዳደር፣ማህበረሰቡራሱህግአክባሪናአስከባሪሆኖእንዲሰለጥንያስፈልጋል፡፡ያስቸግራል፡፡ እንደዛሆኖየሰለጠነዕለትግንህግአስከባሪውመንግስትሳይሆንህዝብራሱይሆናል፡፡የህግአምላክንየሚፈራትውልድይፈጠራል፡፡ያኔነው… የማይታየውወይንምመታየትየማያስፈልገው«Thebestgovernmentwhichgovernsleast»ምናልባትየሚወለደው፡፡ የእግዜርመንግስትበምድርእንደማለትነው፡፡

Read 1439 times Last modified on Wednesday, 30 December 2020 10:01