የ17 አመቷ ታዳጊና የ12ኛ ክፍል ተማሪ በሆነችው ዋዜማ ኤልያስ የተገጠሙ 70 ያህል ግጥሞችን የያዘው “የሱነማዊቷ ቃል” የግጥም መፅሐፍ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ካራቆሬ በሚገኘው አዶ የባህል ምግብ አዳራሽ ተመረቀ። የምርቃቱ አስተባበሪ ጭላሎ ሚዲያ ፕሮዳክሽን እንደገለጸው ታዳጊዋ ግጥሞቹን የጻፈችውና ለህትመት ብርሃን ያበቃችው በኮቪድ 19 ምክንያት ት/ቤት ዝግ በነበረበት ወቅት ያገኘችውን ፋታ ተጠቅማ ነው።
ታዳጊ ዋዜማ በግጥሞቿ ማህበራዊ፣ የፍቅር፣ እና ፍስፍናዊ ጉዳዮችን ዳስሳለች። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ገጣሚያን የስነ-ጽሁፍ ሰዎችና የኪነ-ጠበብ አፍቃሪዎች ታድመው ገጣሚዋን ማበረታታቸውንም የጭላሎ ሚዲያ ፕሮዳክሽን መስራችና ዋና ዳይሬክተር አንዱአለም ጌታቸው ገልጽዋል። መጽሐፉ በ70 ገፅ ተቀንብቦ በ49 ብር ለገበያ ቀርቧል።
Saturday, 19 December 2020 12:18
“የሱነማይቷ ቃል” የግጥም መፅሐፉ ተመረቀ
Written by ናፍቆት ዩሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና