Saturday, 12 December 2020 00:00

የዮናስ ዘውዴ “አልገባኝም" መፅሀፉ ማክሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በወጣቱ የፍልስፍና እና የነገረ መለኮት ምሁር የዮናስ ዘውዴ “አልገባኝም” መጽሀፍ የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ይመረቃል።
በምርቃቱ ላይ በመፅሐፉ ዙሪያ ዳሰሳና ውይይት የሚካሄድ ሲሆን የፍልስፍና ምሁሩ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር)፣ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማየሁ፣ የሙዚቃ ባለሙያው ሰርፀፍሬ ስብሃት፣ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆ፣ ገጣሚ ታገል ሰይፉና ሌሎችም በክብር እንግድነት እንደሚገኙና ሙዚቃ፣ ግጥምና ሌሎች ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶዎች ለታዳሚ እንደሚቀርቡ ታውቋል። ደራሲው ከዚህ ቀደም “ሀምሎክ” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም።


Read 1406 times