Wednesday, 25 November 2020 00:00

ሳይንቲስቶች በማርስ ላይ ከተማ ለመቆርቆር አቅደዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 “ካታላን ኢንስቲቲዩት ኦፍ ስፔስ ስተዲስ” የተባለው የጠፈር ምርምር ተቋም፣ ሳይንቲስቶች በማርስ ፕላኔት ላይ “ኑዋ” የተሰኘች ከተማ ለመቆርቆር ዕቅድ ይዘው እየሰሩ እንደሚገኙ ሲጂቲቼን ዘግቧል፡፡
ሳይንቲስቶቹ በማርስ ላይ አዲስ ከተማ ለመቆርቆር የቀረጹትን “ኑዋ ፕሮግራም” የተሰኘ በአይነቱ አዲስ ፕሮጀክት በመጪዎቹ 30 አመታት ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ማሰባቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ ከተማዋ እስከ 250 ሺህ ነዋሪዎችን የማስተናገድ አቅም እንደሚኖራትም ገልጧል፡፡
የከተማዋን ንድፍ የሚሰራው አልፈርዶ ሙኖዝ የተባለ ታዋቂ አርክቴክት እንደሆነ የገለጸው ዘገባው፣ የከተማዋን አጠቃላይ ግንባታ ለማጠናቀቅ የሚውለውን ወጪ የሚሸፍነው ተቋሙ እንደሆነም አክሎ ገልጧል።


Read 4476 times