Monday, 16 November 2020 00:00

የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ “ታፋኙ” የተሰኘ መጽሐፍ በገቢያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

በአቶ አንዳርጋቸው የተፃፈ “ታፋኙ” የተሰኘው   መጽሐፉ ሰሞኑን ለገበያ ቀረበ፡፡
የአቶ አንዳርጋቸው አፈና የመን ላይ እንዴት፣በማንና በምን ሁኔታ እንደተፈጸመ፤ወደ አዲስ አበባ እንዴት እንደተወሰዱ፤ በአዲስ አበባ እንዴት አንደተጓጓዙ፤ በአዲስ አበባ ድብቅ የአፈና ቤትና በቃሊቲ እስር ቤት የነበራቸውን ሕይወት፣ የአንባቢን ቀልብ በሚይዝ የአተራረክ ዘይቤ  የተሰናዳ ነው ተብሏል፡፡   
በ2010 የአቶ አንዳርጋቸውን መፈታት ወያኔ አጥብቆ በመቃወሙ በኢሕአዴግ ውስጥ ተከስቶ የነበረው ፍጥጫ ምን ይመስል እንደነበርም  ስዕላዊ በሆነ መልኩ ይተርካል፡፡“ታፋኙ” የተሰኘው መጽሀፍ፡፡
በማሳረጊያውም፤ ዓለምን ያስደመመው የኢትዮጵያና የኤርትራ ስምምነት ፍሬያማ መሆን የቻለው፤  ደራሲው ከእስር በተፈቱበት ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በቤተ መንግሥት ባደረጉት ውይይት ምክንያት እንደነበረ ለመጀመሪያ ጊዜ ድርሳኑ ይፋ ያደርጋል፡፡ በ310 ገጾች የተቀነበበው መፅሀፍ፤ በ280 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 22014 times