Saturday, 14 November 2020 10:49

“የሳቅ ንጉሱ” ማስተር በላቸው ግርማ፤ ህይወቱ አስጊ ደረጃ ላይ ነው ተባለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 “የዓለም የሳቅ ንጉስ” የሚል መጠሪያ የተሰጠውና ረጅም ሰዓት በመሳቅና በሌሎች ትዕይንቶች  የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ አገሩን ስሙንና ስራዎቹን ያስመዘገበው ማስተር በላቸው ግርማ፤ ህይወቱ አደጋ ላይ ነው ተባለ።
ማስተር በላቸው በጭንቅላት ዕጢ ህመም ተጠቅቶ የተሳካ ቀዶ ህክምና አድርጎ እንደነበር የሚናገሩት የቅርቡ ሰዎች፤ ሆኖም አሁን ያለበት ሁኔታ ግን አስጊ ስለሆነ ህይወቱን ለመታደግና የተሻለ ህክምና በውጪ እንዲገኝ የወገኖቹን እርዳታ ይሻል ተብሏል።
ማስተር በላቸውን ለማገዝ የሚውል የገቢ ማስባሰቢያ መርሃ ግብር ዛሬ  (ቅዳሜ) በአብርሃም ግዛው ኢንተርቴይመንት አዘጋጅነት በስካይ ላይት ሆቴል የተዘጋጀ ሲሆን የሳቅ ንጉሱን መርዳት የሚፈልግ በስነ-ስርዓቱ ላይ በስካይ ላይት ሆቴል ተገኝቶ የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ሆነው በመርሃ ግብሩ መሳተፍ ለማይችሉ በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በስሙ በተከፈተው 1000058068277 ማስተር በላቸው ግርማ ብለው ድጋፍ እንዲያደርጉና በስልክ ለማነጋገር ደግሞ በ0911-24 41 01 ደውሎ የሞራልና የስነ-ልቦና ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻ ታውቋል። ማስተር በላቸው በአሁኑ ሰዓት በህመም በአልጋ ላይ ተኝቶ እንደሚገኝና ከወገኖቹ ድጋፍ እንደሚሻ ለማወቅ ተችሏል።

Read 11948 times